Logo
SeledaPost
#ጤናመረጃ

ሙዝ ለጤናችን የሚሰጠን 12 አስደናቂ ጥቅሞች!

ሙዝ በንጥረ ነገር ይዘታቸው ከበለፀጉ ፍራፍሬዎች አንድ ሲሆን በውስጡ በርከት ያሉ እንደ ማግኒዚየም ፣ ፓታሲየም ፣አይረን፣ ዚንክ፣ አዮዲንና ቫይታሚን ኤ፣ቢ፣ኢ፣ኤፍን ይዛል።

1- የሀይል ምንጭ ነው:- ሙዝ በውስጡ ቫይታሚን፣ሚኒራል እና ካርቦሀይድሬት በመያዙ ሀይል ለማግኘት ይጠቅማል፡፡

2- ለምግብ መንሸራሸር ይጠቅማል:- ይህም የሚሆነው ሙዝ በውስጡ የቃጫ ባህሪ(ፋይበርነት) ስላለው ነው፡፡

3- የጨጓራ ህመምን ያስታግሳል:- ጨጓራ ጠንካራ ግድግዳ እንዲኖረው እና በጨጓራ ውስጥ ያለውን አሲድነት በመቀነስ ህመምን ያስታግሳል፡፡

4- የልብን ጤንነትን ይጠብቃል:- ሙዝ በፖታሲየም የበለፀገ ስለሆነ ይህም ለልብ ጤንነት አስፈላጊ ነው፡፡

5- ክብደትን ለመቀነስ ይረዳል:- ሙዝ በውስጡ አነስተኛ ቅባት እንደዚሁም ብዙ ፋይበር ሰለያዘ ክብደትን ለመቀነስ ይረዳል፡፡

6- አኔሚያን ለማከም ይረዳል:- ሙዝ በውስጡ በዛ ያለ የብረት ማእድን ስለያዘ ይህም የቀይ የደም ሴልን ማነስ ይከላከላል፡፡

7.ነብሰጡሮችን ከህመም ይታደጋል:- ነብሰጡር ሴቶችን የሚያጠቃ የጠዋት ህመም የሚባለውን ለማከም ይረዳል፡፡

8.የአይንን ጤና ያሻሽላል:- ሙዝ ቫይታሚን ኤን ስለያዘ የአይን በሽታን ይከላከላል፡፡

9.በወባ ትንኝ የተነደፈን ይፈውሳል:- የተነደፈበት ቦታ በሙዝ ልጣጭ በማሸት ከህመሙ ይፈውሳል፡፡

10.ጥርስን ያነጣል፦ በሙዝ ልጣጭ ጥርስዎን ሁልጊዜ ጥርስዎን ሲፍቁ ለአስደናቂ ፈገግታ ይኖርዎታል።

11.የተጎድ የሰውነት ቆዳን ያስተካክላል፣ የፊት መሸብሸብ እና የቆዳ መሰንጠቅን ይከላከላል።

12.ክንታሮትን ያድናል:- ሙዝ በፓታሲየም የበለጸገ ስለሆነ ክንታሮትን የማዳን አቅም አለው።
ጠቃሚ ነውና ለወዳጆ ያካፍሉ! ሼር

seledadotio
seledadotio
6 months ago

No replys yet!

Be the first to share what you think — your comment will appear here.