“አርሰናል የእንግሊዝም የአውሮፓም ምርጡ ቡድን ነው” — ፔፕ ጋርዲዮላ
#ethiopia | የማንችስተር ሲቲው ስኬታማ አሰልጣኝ ፔፕ ጋርዲዮላ፣ መድፈኞቹ ባለፉት ጥቂት ዓመታት የገነቡት ቡድን እጅግ የሚደነቅ መሆኑን ገልጸው የአውሮፓ ምርጡ ስብስብ ነው ሲሉ አወደሱ።
ጋርዲዮላ ስለ አርሰናል ወቅታዊ አቋም በሰጡት አስተያየት “አርሰናል የእንግሊዝም የአውሮፓም ምርጡ ቡድን ነው፤ ቁጥሮችም የሚያሳዩት ይህንኑ ነው” ብለዋል። ቡድኑ በተለይም የሚያሳየው ወጥነት (Consistency) ዋነኛ ጥንካሬው መሆኑንና እነሱን ማሸነፍ እጅግ ፈታኝ እየሆነ መምጣቱን አክለዋል።
አሰልጣኙ አርሰናል አሁን ለደረሰበት ደረጃ ትልቅ አድናቆት ሊሰጠው እንደሚገባ ጠቁመው፣ ሲቲም በሳምንቱ አጋማሽ ጨዋታዎች የሚሳተፍበትና አርሰናል አሁን ያለበት ደረጃ ላይ ቢሆን እንደሚመኙ በንግግራቸው ፍንጭ ሰጥተዋል።
በተጨማሪም ከካራባኦ ካፕ የፍፃሜ ጨዋታ በፊት በቡድናቸው ስኬት ላይ ጥርጣሬ የነበራቸውን ወገኖች በማስታወስ፣ አርሰናል የገነባው ስብስብ አሁን ላይ ለማንም የማይበገር መሆኑን በአፅንኦት ገልጸዋል።
Getu Temesgen - (ጌጡ ተመስገን)
#getutemesgen #getu #tikvahsport #arsenal #mancity #guardiola #premierleague #footballnews #አርሰናል #ማንችስተርሲቲ #ጋርዲዮላ #እንግሊዝፕሪሚየርሊግ #ስፖርትዜና

4 months ago