Logo
Getu Temesgen
ተስፋ አልባ የፍቅር ስሜት ምንድነው?
What is a Hopeless Romantic!
#ethiopia | ማፍቀር ተፈጥሯዊ ነው። ተስፋ አልባ የፍቅር ስሜት ደግሞ፤ ቅዠት ውስጥ ሆኖ እንደመቃተት ያለ ስሜት በመሆኑ፤ ሃሳባዊነት ላይ የተንጠለጠለ ወይም ዘለቄታ የሌለው የእውር ድንብር ጉዞ ነው።

ተስፋ አልባ የፍቅር ስሜት ውስጥ ያሉ ሰዎች ባህርይ:-

1. ለፍቅር ባላቸው ጥልቅ ስሜት ለህይወት ጥሩ አመለካከት አላቸው።

2. ልባቸው ስስ እና ለመጠመድ ቅርብ ነው።

3. የኔ የሚሉትን 'ፍቅር' ያገኙ ሲመስላቸው ለማቆየት ማንኛውንም ነገር ከማድረግ አይመለሱም።

4. ፍቅርን በተሳሳተ ቦታ እና ጊዜ ያሳድዳሉ።

5. ማንንና ምን እንደሚፈልጉ ቢያውቁም፤ በሚደርስባቸው ነገር ልባቸው እንዳዘነ ነው።
#ከተስፋ -ቢስ ፍቅር ለማምለጥ ምን ማድረግ አለብዎ?

1. ፍፁምነትን ማሳደድ ያቁሙ:-

"ከሰው ስህተት ከብረት ዝገት!..." እንዲሉ አለም ከስህተት የፀዳች አይደለችምና እውነትዎን አርቀው አይስቀሉ። ፍፁምነት ከአምላክ እንጂ ከሰው አይጠብቁ።

2. ፍቅርን ለማግኘት ከአቅምዎ በላይ ዋጋ አይክፈሉ:-

ለፍቅር ዋጋ መክፈል ያስፈልግ ይሆናል፤ሆኖም የጀመሩት ወይም ያሰቡት ፍቅር ዋጋ የሚያስከፍል ስለመሆኑ እና አለመሆኑ ማሰብና ማገናዘብ ይሻል።

3. ፈላጊ እንጂ ተፈላጊ ካልሆኑ ይንቁ:-

ፍቅር ፈላጊ መሆን ብቻ ሳይሆን ተፈላጊ መሆንን ያጠቃልላል። ፈላጊ ብቻ ከሆኑ ፍቅርን የተሳሳተ ቦታ እየፈለጉት ነውና ይንቁ።

4.ጤናማ ባልሆነ ግንኙነት ውስጥ አይቆዩ:-

እውነተኛ ፍቅር ጤናማ ነው። ውስጡ ንዴት፣ ብስጭት፣ቁጣ እና ፀፀት... የለበትም። ጤናማ ባልሆነ ግንኙነት ውስጥ መሆንዎን ካወቁ በአስቸኳይ ያምልጡ።

ሰላም ለኢትዮጵያ!...
ዳዊት ይዘንጋው /ዳይተም/

6 months ago

No replys yet!

Be the first to share what you think — your comment will appear here.