ከየኔታ ሚዲያ ለክቡራን ተከታታዮቻችንና ለጥበብ ወዳጆች የተሰጠ ማብራሪያ
አርቲስት ቴዎድሮስ ካሳሁን (ቴዲ አፍሮ) ለኢትዮጵያና ለኢትዮጵያውያን የጥበብ ምልክት፣ የፍቅርና የአንድነት ድምፅ መሆኑን የየኔታ ሚዲያ ቤተሰቦች በሙሉ ልብ እናምናለን።
ባለፈው በሰራነው ዘገባ ላይ የቀረበው አስተያየትም ካለን ጥልቅ አክብሮትና "ለታላቅ አርቲስት ታላቅ ስራ ይገባል" ከሚል በጎ ቅናት እንጂ፣ በምንም መልኩ አርቲስቱን ለመንካት ወይም ስራውን ለማሳነስ የታለመ እንዳልሆነ እንድትረዱልን እንወዳለን።
ጥበብ ዘርፈ ብዙ እንደመሆኑ የቴዲ ወርቃማ ድምፅና ግጥም ከዘመኑ የቴክኖሎጂ ዕድገት ጋር ተባብሮ ሲቀርብ ክብሩን ይበልጥ ያገዝፈዋል የሚል እምነት አለን።
አስተያየታችን የጥላቻ ሳይሆን የቴዲ አፍሮ ስራዎች በዓለም አቀፍ መድረክ ሲታዩ በምስል ጥራትም (Visual quality) ጭምር ኢትዮጵያን እንዲያስከብሩ ካለን ጽኑ ፍላጎት የመነጨ ነው።
ቴዲ ለእኛ ከድምፃዊነት በላይ የታሪክና የማንነት መገለጫችን ነው።
በመሆኑም ለደጋፊዎቹ ለሰጣችሁን አስተያየት እናመሰግናለን፤ ፍቅራችሁንና ለአርቲስቱ ያላችሁን ተቆርቋሪነት እንረዳለን። እኛም ከእናንተ በላይ ለቴዲ ስኬት የምንመኝ መሆናችንን እንገልጻለን።
ውዱ የኢትዮጵያ ልጅ አርቲስት ቴዲ አፍሮ "ኢቶሪካ" (Etorika) የተሰኘው አዲሱ አልበምህ እንደ ቀደሙት ስራዎችህ ሁሉ በኢትዮጵያ ምድር ላይ ታሪክ ሰርቶ፣ የሕዝባችንን ልብ በደስታና በፍቅር እንዲሞላ ከልብ እንመኛለን።
የኔታ ሚዲያ ሁሌም የጥበብና የጥበብ ባለሙያዎች ደጋፊ ሆና ትቀጥላለች።
ሐሙስን በጉጉት እንጠብቃለን!
መልካም በዓል

2 months ago