Logo
FastMereja
ድምጻዊ ያሬድ ነጉ ለትንሳኤ በዓል የእንኳን አደረሳችሁ መልዕክት አስተላለፈ

​#fastmereja I ታዋቂው ድምጻዊ ያሬድ ነጉ መለሰ የጌታችን የመድኃኒታችን የኢየሱስ ክርስቶስን የትንሳኤ በዓል በማስመልከት በሀገር ውስጥና በውጭ ለሚገኙ ኢትዮጵያውያን የእንኳን አደረሳችሁ መልዕክት አጋርቷል።

​ድምጻዊው ባስተላለፈው መልዕክት በዓሉ የሰላም እንዲሆን ከመመኘት ባለፈ፣ በአሁኑ ወቅት በሀገሪቱ ያለውን ወቅታዊ ሁኔታ የሚዳስስ ሃሳብ አንስቷል። "በሀገራችን የእናቶች እንባ በዛ" ያለው ያሬድ፣ በግፍ እየሞቱ ላሉ ወገኖች "በቃ" የሚባልበት እና ለቅሶ የሚያበቃበት ትንሳኤ እንዲሆን ያለውን መልካም ምኞት ገልጿል።

​ያሬድ ነጉ በመልዕክቱ ማጠቃለያ ላይ ለመላው የክርስትና እምነት ተከታዮች መልካም በዓል እንዲሆንላቸው ተመኝቷል።

​ሚያዝያ 4 ቀን 2018 ዓ.ም.

2 months ago

No replys yet!

Be the first to share what you think — your comment will appear here.