የሩሲያው ፕሬዝዳንት ቭላድሚር ፑቲን ለኦርቶዶክስ ክርስቲያኖች የትንሳኤ በዓል የእንኳን አደረሳችሁ መልዕክት አስተላለፉ
#fastmereja I የሩሲያው ፕሬዝዳንት ቭላድሚር ፑቲን የጌታችን የመድኃኒታችን የኢየሱስ ክርስቶስን የትንሳኤ በዓል በማስመልክት ለሀገሪቱ የኦርቶዶክስ ክርስቲያኖችና በዓሉን ለሚያከብሩ ሩሲያውያን በሙሉ የእንኳን አደረሳችሁ መልዕክት አስተላልፈዋል።
ፕሬዝዳንቱ በመልዕክታቸው፣ የትንሳኤ በዓል በሚሊዮኖች በሚቆጠሩ ሰዎች ልብ ውስጥ የእውነተኛ ደስታ፣ የህይወት ድል፣ የፍቅር፣ የደግነት እና የፍትህ ተስፋን የሚሞላ ታላቅ በዓል መሆኑን ገልጸዋል። የሩሲያ ኦርቶዶክስ ቤተክርስቲያን እና ሌሎች የክርስትና እምነት ተከታዮች የሀገሪቱን ታሪካዊ እና ባህላዊ ቅርሶች በመጠበቅ፣ የቤተሰብ ተቋምን በማጠናከር እና ወጣቱን ትውልድ በማነጽ ረገድ የሚጫወቱት ሚና ከፍተኛ መሆኑንም አክለዋል።
በተጨማሪም የሃይማኖት ድርጅቶች ከመንግስት ጋር የሚያደርጉት ገንቢ ትብብር፣ የሃይማኖቶች እና የብሄረሰቦች ውይይት እንዲጠናከር የሚያደርጉት ጥረት እንዲሁም "ልዩ ወታደራዊ ዘመቻ" ለሚሳተፉ ወታደሮችና ለቤተሰቦቻቸው የሚያደርጉት ድጋፍ የሚደነቅ መሆኑን ፕሬዝዳንት ፑቲን በመልዕክታቸው ጠቁመዋል። ፕሬዝዳንቱ በመጨረሻም ለህዝባቸው ጤና እና ብልጽግናን ተመኝተዋል።
ሚያዝያ 4 ቀን 2018 ዓ.ም.

2 months ago