በአዲስ አበባ የትንሳኤ በዓልን ምክንያት በማድረግ የዘጠኝ ዙር መድፍ ተኩስ እንደሚከናወን ተገለጸ
የኢፌዴሪ መከላከያ ሚኒስቴር የ2018 ዓ.ም የትንሳኤ በዓልን ምክንያት በማድረግ ነገ ከለሊቱ 9፡00 ሰዓት ላይ ዘጠኝ ጊዜ የመድፍ ተኩስ እንደሚከናወን አስታውቋል።
በመከላከያ ስፖርትና ኪነ ጥበባት ስራዎች ማዕከል በኩል የወጣው ይሄው መረጃ እንደሚያመለክተው፣ የተኩስ ስነ-ስርዓቱ የተለመደውን የበዓል አከባበር ስነ-ስርዓት ተከትሎ የሚከናወን ነው።
የአዲስ አበባ ፖሊስ ጠቅላይ መምሪያ በበኩሉ ህብረተሰቡ ስለ መድፍ ተኩሱ አስቀድሞ ተገቢው መረጃ እንዲኖረው ያሳሰበ ሲሆን፣ ነዋሪዎች ከለሊቱ ዘጠኝ ሰዓት ጀምሮ የሚሰማውን ድምፅ በበዓል አከባበር ስነ-ስርዓት ምክንያት የሚከናወን መሆኑን አውቆ ያለምንም ስጋትና መደናገጥ በዓሉን እንዲያከብር ጥሪውን አቅርቧል።
ፖሊስ ለመላው የክርስትና እምነት ተከታዮችም መልካም የበዓል ምኞቱን ገልጿል።
seledadotio

2 months ago