ድንገተኛ አደጋ ሕይወታቸው አለፈ
#fastmereja I የመከላከያ ኮንስትራክሽን ኢንተርፕራይዝ በኢትዮጵያ ፌዴራል ፖሊስ የምስራቅ ቀጠና የፈጥኖ ደራሽ ፖሊስ ማዕከል ግንባታ ፕሮጀክት ላይ ሲያገለግሉ የነበሩ ሶስት ከፍተኛ የሥራ መሪዎችና ባለሙያዎች በድንገተኛ የመኪና አደጋ ሕይወታቸው ማለፉን አስታውቋል።
በአደጋው ሕይወታቸው ያለፈው የሥራ መሪዎችና ባለሙያዎች፦
ሌ/ኮሎኔል ኢንጂነር አዲሱ ጎኣ (የፕሮጀክቱ ሥራ አስኪያጅ)
አቶ ሳሙኤል ማሞ (የፕሮጀክቱ ሾፌር)
ኢንጂነር በረከት ኡታ (ከኢትዮጵያ ኢንጂነሪንግ ኮርፖሬሽን የፕሮጀክቱ አማካሪና ተቆጣጣሪ መሐንዲስ) መሆናቸው ተረጋግጧል።
ኢንተርፕራይዙ ባወጣው የሀዘን መግለጫ፣ ሟቾቹ ተቋማዊና ሀገራዊ ግዳጃቸውን በላቀ የሥራ ዲሲፕሊንና በትጋት ሲወጡ የነበሩ መሆናቸውን ገልጾ፤ በደረሰው ድንገተኛ ሞት የተሰማውን ጥልቅ ሀዘን ገልጿል። ለሟች ቤተሰቦች፣ ወዳጅ ዘመዶችና ለሥራ ባልደረቦቻቸው መፅናናትን ተመኝቷል።
ሚያዝያ 03 ቀን 2018 ዓ.ም

2 months ago