አንጋፋዋ ዲፕሎማት አምባሳደር ቆንጂት ሥነ-ጊዮርጊስ ከዚህ ዓለም በሞት ተለዩ
#ethiopia | በኢትዮጵያ የዲፕሎማሲ ታሪክ ውስጥ የጎላ አሻራ ያሳረፉት አንጋፋዋ ዲፕሎማት አምባሳደር ቆንጂት ሥነ-ጊዮርጊስ ባጋጠማቸው የጤና እክል በሕክምና ሲረዱ ቆይተው ከዚህ ዓለም በሞት መለየታቸው ተሰማ።
አምባሳደር ቆንጂት ከ1950ዎቹ አጋማሽ ጀምሮ በውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ውስጥ ከዴስክ ኦፊሰርነት አንስቶ እስከ ከፍተኛ ኃላፊነት ድረስ ሀገራቸውን በታማኝነት አገልግለዋል። በተለይም የቀድሞው የአፍሪካ አንድነት ድርጅት (የአሁኑ የአፍሪካ ህብረት) ከመመስረቱ አንድ ዓመት ቀደም ብለው ወደ ዲፕሎማሲው ዓለም የተቀላቀሉ ሲሆን፤ በአፍሪካ ቀዳሚ ከሆኑ ሴት ዲፕሎማቶች መካከል በግንባር ቀደምትነት ስማቸው ይጠቀሳል።
ከአምባሳደር ዮዲት እምሩ ቀጥሎ የኢትዮጵያ ሁለተኛዋ ሴት አምባሳደር በመሆን ታሪክ የሰሩት አምባሳደር ቆንጂት፤ በካይሮ፣ ኦታዋ፣ ቴል አቪቭ እና ቪየና በሚገኙ የኢትዮጵያ ሚሲዮኖች በባለሙሉ ስልጣን አምባሳደርነት ሀገራቸውን ወክለዋል። በተጨማሪም በአፍሪካ ሕብረት እና በተባበሩት መንግሥታት የአፍሪካ ኢኮኖሚክ ኮሚሽን የኢትዮጵያ ቋሚ መልዕክተኛ ሆነው በብቃት ሰርተዋል።
በቀጠናው ሰላም ግንባታም ከፍተኛ ሚና የነበራቸው ሲሆን፤ ከሰኔ 2009 እስከ መስከረም 2011 ዓ.ም ድረስ ኢጋድ ባመቻቸው የደቡብ ሱዳን የሰላም ስምምነት ሂደት ላይ በልዩ አማካሪነት በማገልገል የዲፕሎማሲ ልምዳቸውን አበርክተዋል።
አምባሳደሯ ለግማሽ ክፍለ ዘመን ገደማ ለሀገራቸው እና ለአህጉራቸው ላበረከቱት የላቀ የዲፕሎማሲ አገልግሎት ከዚህ ቀደም በሀገር ደረጃ ከፍተኛ ዕውቅና እና ሽልማት ተበርክቶላቸው እንደነበር ይታወሳል ሲል ሸገር ኤፍ ኤም ዘግቧል።
Getu Temesgen - (ጌጡ ተመስገን)
#getutemesgen #getu #ኢትዮጵያ #አምባሳደር_ቆንጂት #ዲፕሎማሲ #ውጭ_ጉዳይ_ሚኒስቴር #የአፍሪካ_ህብረት #ethiopia #ambassadorkonjit #diplomacy

6 months ago