የኤርትራ እና የትግራይ ህዝቦች ወንድማማችነትን የሚያጠናክር መድረክ በሸራሮ ከተማ ተካሄደ
#fastmereja I በትግራይ ክልል ሰሜናዊ ምዕራብ ዞን በምትገኘው ሸራሮ ከተማ የኤርትራ እና የትግራይ ህዝቦችን ታሪካዊ ትስስር ለማደስና ወንድማማችነትን ለማጠናከር ያለመ የህዝብ ለህዝብ መድረክ ትናንት እና ዛሬ መካሄዱ ተገለጸ።
ትግራይ ቲቪ እንደዘገበው ከሆነ፣ ትናንት መጋቢት 27 ቀን 2018 ዓ.ም በተከበረው የሆሳዕና እና የመድኃኒዓለም በዓላት ላይ ለመታደም ከ700 በላይ ኤርትራውያን ወደ ሸራሮ ከተማ ገብተዋል። እነዚህ ወገኖች ከበዓሉ ተሳትፎ ባሻገር፣ ከምዕራብ እና ከሰሜን ምዕራብ ትግራይ ተፈናቅለው በሸራሮ ለሚገኙ ተፈናቃዮች የሚሆን የእህል እርዳታ ይዘው መቅረባቸው የሁለቱን ህዝቦች የቆየ የመረዳዳት ባህል በተግባር ያሳየ ሆኗል።
በሃይማኖት አባቶችና በሀገር ሽማግሌዎች አስተባባሪነት በተዘጋጀው በዚህ መድረክ፣ በጦርነትና በድንበር መዘጋት ምክንያት ለረጅም ዓመታት ተራርቀው የቆዩ ቤተሰቦችና የቅርብ ዘመዳሞች ተገናኝተው ደስታቸውን ገልጸዋል። በዛሬው እለት (መጋቢት 28 ቀን 2018 ዓ.ም) የቀጠለው መርሃ ግብርም የጋራ ሃይማኖታዊ ስነ-ስርዓቶችንና የህዝብ ለህዝብ ውይይቶችን ያካተተ ሲሆን፣ ይህም በሁለቱ ህዝቦች መካከል ያለው ግንኙነት ወደ ቀድሞ ታሪካዊ ይዘቱ እየተመለሰ መሆኑን የሚያመላክት እንደሆነ ተጠቅሷል።
መጋቢት 28 ቀን 2018 ዓ.ም

2 months ago