ሆሳዕና ለዳዊት ልጅ፣ በጌታ ስም የሚመጣ የተባረከ ነው🙏
ልበ አምላክ ቅዱስ ዳዊት በመዝሙር 117÷25-26 “አቤቱ እባክህ አሁን አድን፣ አቤቱ እባክህ አሁን አቅና፣ በእግዚአብሔር ስም የሚመጣ ቡሩከ ነው፡፡” በማለት ይናገራል፡፡ ነቢየ እግዚአብሔር ቅዱስ ዘካርያስም በትንቢቱ 9÷9 ደግሞ “አንቺ የጽዮን ልጅ ሆይ እጅግ ደስ ይበልሽ፤ አንቺ የኢየሩሳሌም ልጅ ሆይ እልል በዪ፤ እነሆ ንጉሥሽ ጻድቅና አዳኝ ነው፤ ትሑትም ሆኖ በአህያም በአህያይቱም ግልገል በውርንጫይቱ ተቀምጦ ወደ አንቺ ይመጣል፡፡” ተብሎ ተጽፏል፡፡ ትንቢቱ ይፈጸም ዘንድም በዕለተ ሆሳዕና ጌታችን በአህያ ላይ ተቀምጦ ወደ ኢየሩሳሌም ገባ፡፡ ሆሳዕና የሚለው ቃል ቃል ከዕብራይስጡ “ሆሼዕናህ” የመጣ ሲሆን ትርጉሙም እባክህ አሁን አድን ማለት ነው፡፡ ሆሣዕና ማለት መድኃኒት ወይም አቤቱ አሁን አድን ማለት ነው፡፡
ከትንሣኤ በዓል አንድ ሳምንት ቀድሞ የሚከበርና ከጌታችን ዘጠኙ ዓበይት በዓላት አንዱ ነው። ጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ በአህያ ጀርባ ተቀምጦ ወደ ኢየሩሳሌም ሲገባ የሚቀድሙትና የሚከተሉት ሕዝብ በተለይም አእሩግና ሕፃናት ሆሳዕና ለዳዊት ልጅ፣ በጌታ ስም የሚመጣ የተባረከ ነው፣ ሆሳዕና በአርያም በማለት ጌታችንን በክብር መቀበላቸው የሚታወስበት በዓል ነው፡፡ ከቅዱስ ያሬድ ሲወርድ ሲዋረድ የመጣው ዜማ በሌሊቱ ማህሌት ይዘመራል። ደግሞም ዕለቱ የጸበርት ወይም የዘንባ እሑድ ይባላል፡፡ ይህም ከአባታችን ከይስሐቅ ልደት ጋር ተያይዞ የመጣ ነው፡፡ ሣራ የወላድነት ዕድሜዋን ከጨረሰች በኋላ ሁሉን ቻይ እግዚአብሔር ይስሐቅን ሲሰጣት ዘመዶቿ በደስታ የዘንባባ ዝንጣፊ በመያዝ የጎበኟትን አምላክ አመስግነዋል፡፡
አንድም እስራኤል ከአስከፊው የግብፃውያን አገዛዝ ተላቀው ባሕረ ኤርትራን በደረቅ ሲሻገሩ የተሰማቸውን ልዩ ደስታ የዘንባባ ዝንጣፊ በመያዝ እግዚአብሔርን አመስግነዋል፡፡ እስራኤል ዘነፍስ የምንባል እኛም ዕለቱን ዘንባባ /ጸበርት/ በግንባራችን በማሰር በዓሉን በየዓመቱ እናከብራለን፡፡ በክብርና በምስጋና ወደ ኢየሩሳሌም ሲገባ ከተማዋ በዝማሬና በአመስጋኞች ጩኸት ተናወጠች፡፡ የሕዝቡ ጩኸትና ደስታ ያበሳጫቸው ፈሪሳዊያንና አይሁድ የሚያመሰግኑትን ዝም እንዲያሰኝ ጌታችንን ቢጠይቁትም በነቢዩ ዳዊት መዝ 8÷2 “ከሚጠቡ ሕፃናትና ከልጆች ምሥጋናን አዘጋጀህ” ተብሎ እንደተጻፈ “እነዚህ ዝም ቢሉ ድንጋዮች ያመሰግኑኛል” ብሎ መልሶላቸዋል፡፡ ምስጋና ዘወትር ከአፋቸው የማይለያቸውን ገዳማውያንን እናስብ፤ ገዳማቸውን እንደግፍ በዓታቸውን እናጽና፡፡
ድጋፍ ለማድረግ:- ሙትአንሳ ማር ቅዱሰ ሚካኤል አንድነት ገዳም
ኢትዮጲያ ንግድ ባንክ
1000442598391
ወይም
አቢሲኒያ ባንክ
141029444
ለበለጠ መረጃ:- 09 38 64 44 44/0918077957

2 months ago