Logo
Getu Temesgen
አሚጎስ አርቲስት ግሩም ኤርሚያስን የብራንድ አምባሳደር አድርጎ ሾመ

​#ethiopia | ​አሚጎስ የገንዘብ ቁጠባና ብድር የኃላፊነቱ የተወሰነ የህብረት ስራ ማህበር በስራ ላይ የቆየበትን 13ኛ ዓመት የምስረታ በዓል አስመልክቶ ተዋናይና ዳይሬክተር ግሩም ኤርሚያስን የብራንድ አምባሳደር አድርጎ ሾመ።

ማህበሩ ባለፉት አስራ ሶስት ዓመታት በፋይናንስ ዘርፍ ማህበረሰቡን ተጠቃሚ የሚያደርጉ በርካታ ስኬቶችን ያስመዘገበ ሲሆን አሁን ላይም ከአገር አቀፍ እውቅና አልፎ የዓለም አቀፍ የህብረት ስራ ማህበራት ጥምረት (ICA) እና የአፍሪካ የህብረት ስራ ማህበራት ኮንፌዴሬሽን (ACCOSCA) አባል በመሆን የላቀ ተደራሽነትን መፍጠር ችሏል።

​የማህበሩ ስራ አስኪያጅ አቶ ፍፁም አብርሃም በዚሁ የፊርማ ስነስርዓት ላይ እንደገለጹት አሚጎስ የፋይናንስ ተደራሽነት አነስተኛ በሆነባቸው አካባቢዎች ላይ ትኩረት በማድረግ ማህበረሰቡን በቁጠባና በብድር አገልግሎት ለመደገፍ በትጋት ሲሰራ ቆይቷል።

ማህበሩ በዲጂታል አሰራር ዘምኖ አነስተኛ የንግድ ስራ ላይ የተሰማሩ ዜጎችን፣ ሴቶችንና ወጣቶችን የብድር ተጠቃሚ በማድረግ ረገድ ከፍተኛ ሚና እየተጫወተ እንደሚገኝም አቶ ፍፁም አክለው ገልጸዋል።

ተቋሙ ከአገር ውስጥ አልፎ በዓለም አቀፍ ደረጃ የሚገኙ ምርጥ ተሞክሮዎችን ወደ አገር ውስጥ በማስገባት የገንዘብ ቁጠባና ብድር ማህበራት ንቅናቄ ውስጥ ግንባር ቀደም ተዋናይ መሆን እንደቻለ ስራ አስኪያጁ በኩራት ተናግረዋል።

​አሚጎስ የገንዘብ ቁጠባና ብድር የኃላፊነቱ የተወሰነ የህብረት ስራ ማህበር አምባሳደር ሆኖ የተመረጠው አንጋፋው የኪነ-ጥበብ ባለሙያ ግሩም ኤርሚያስ በበኩሉ አሚጎስ ማህበራዊ ኃላፊነቱን ለመወጣት የሚያደርገው ጥረት እጅግ የሚያስደንቅ መሆኑን ገልጿል።

አሚጎስ የገንዘብ ቁጠባና ብድር የኃላፊነቱ የተወሰነ የህብረት ስራ ማህበር አምባሳደር ሆኖ መመረጡ ታላቅ ደስታ እንደፈጠረለት የገለጸው ግሩም ኤርሚያስ፣ በቀጣይም ማህበረሰቡ ከአሚጎስ ጋር በመሆን የቁጠባ ባህሉን እንዲያሳድግና በጋራ ለመስራት የበኩሉን ጥረት እንደሚያደርግ ቃል ገብቷል።

Getu Temesgen - (ጌጡ ተመስገን)
#getutemesgen #getu #ጌጡ

📷 ከበደ መክብብ

​#amigos #finance #cooperative #ethiopia #grümErmias #savingsandcredit #empowerment #brandambassador

6 months ago

No replys yet!

Be the first to share what you think — your comment will appear here.