Logo
SeledaPost
የሶማሊያ ፌዴራል ኃይሎች ባይዶአን ተቆጣጠሩ

የፌዴራል ጦር እና ተጓዳኝ የታጠቁ ቡድኖች ባይዶአን መቆጣጠራቸውን ተከትሎም የሶማሊያ የደቡብ ምዕራብ ግዛት ፕሬዝዳንት አብዲአዚዝ ሐሰን ላፍታጋሪን ሥልጣናቸውን መልቀቃቸውን አስታውቀዋል።

በባይዶአ በነበረው ግጭት ቢያንስ የሁለት ሰዎች ሕይወት ሲያልፍ፤ 25 ሌሎች ደግሞ ቆስለዋል።

ላፍታጋሪን በይፋዊ የፌስቡክ ገጻቸው ባወጡት አጭር መግለጫ፣ መልቀቂያቸው ወዲያውኑ ተግባራዊ እንደሚሆን ገልጸዋል። ሆኖም ስለ ውሳኔው ዝርዝር ማብራሪያ አልሰጡም፤ በአሁኑ ወቅት የት እንደሚገኙም የታወቀ ነገር የለም።

ሰኞ የሶማሊያ ብሔራዊ ጦር ኃይሎች ከታጠቁ ሚሊሻዎች ጋር በመሆን ወደ ባይዶአ የገቡ ሲሆን፣ የፖሊስ ጣቢያውን እና ዋና ዋና የንግድ ማዕከላትን ጨምሮ ቁልፍ ተቋማትን መቆጣጠራቸው ተዘግቧል።

ለላፍታጋሪን ታማኝ የሆኑ የክልሉ ኃይሎች ከተማዋን ለቀው መውጣታቸው የተገለጸ ሲሆን፤ አውሮፕላን ማረፊያውን እና የፕሬዝዳንቱን ጽሕፈት ቤት ጨምሮ ስትራቴጂካዊ ስፍራዎች በአፍሪካ ህብረት የሚመራው ኃይል ጥበቃ ስር እንደነበሩ ትላንት መዘገቡ ይታወሳል።

የፕሬዝዳንቱን መልቀቅ ተከትሎ የደቡብ ምዕራብ ግዛት የፋይናንስ ሚኒስትር አህመድ መሐመድ ሁሴን ተጠባባቂ ፕሬዝዳንት ሆነው ተሰይመዋል።

seledadotio
seledadotio
2 months ago

No replys yet!

Be the first to share what you think — your comment will appear here.