"በስራና ክህሎት ሚኒስቴር በደል ተፈፅሞብናል"
ኬዲ ሪልስቴት ዴቨሎፐርስ አክስዮን ማህበር
ከ11 ዓመታት በፊት በካዛንቺስ ቁጥር 2 መልሶ ማልማት ከይዞታቸው ተፈናቅለዋል፤ቁጥራቸው 63 የሆኑ ነዋሪዎች፡፡እነዚህ የግል ባለይዞታዎች ኬዲ ሪል ስቴት ዴቨሎፐርስ አክስዮን ማኅበርን አቋቁመዋል፡፡
የአዲስ አበባ ከተማ ባወጣው LDP መሰረት የከተማው ካቢኔ ነዋሪዎች መልሰው ማልማት እንዲችሉ 5533 ካሬ ሜትር የተፈቀደላቸው ሲሆን ከዚህ ውስጥ ለኮሪደር ልማት ተቀንሶ፣ በውል የተፈቀደ 5333 ካሬ ሜትር ኤሌክትሮኒክስ ካርታ ሚያዚያ 16/2017 ዓ.ም የይዞታ ማረጋገጫ ተሰጥቷቸዋል፡፡
ከተሰጠን መሬት ውስጥ 970 ካ.ሜ የሚሆነው መሬት በቀድሞው የማህበራዊ ጉዳይ ሚኒስቴር በአሁኑ የስራና ክህሎት ሚኒስቴር በካርታችን ላይ ተጠቃሏል ያሉት የሪል ስቴቱ የቦርድ ሰብሳቢ አቶ ንጉሴ ጤና፣የልማት ተነሺዎች ክፍለከተማው ካርታ ሲሰጠን ያልፀዳውን 970 ካሬ ሜትር የሚሆነው መሬት አፅድቶ ሊያስረክበን ተዋውለን ነበር።
በተሰጠን ይዞታ ላይ ከ2013 ዓ.ም ጀምሮ ላልተረከብረው 970 ካ.ሜ መሬት ጭምር በየዓመቱ ከ1ሚሊዮን ብር በላይ የሊዝ ክፍያ እየከፈልን ነው ብለዋል።
በውል የተሰጠን የኤሌክትሮኒክስ ካርታ ፀድቶ እንዲሰጠን ለቂርቆስ ክፍለከተማ የመሬት ልማትና አስተዳደር ፅ/ቤት፣ ለአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር መሬት ልማትና አስተዳደር ቢሮ፣ለአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ም/ቤት በተደጋጋሚ ጠይቀናል።የቂርቆስ ክፍለከተማ የመሬት ልማትና አስተዳደር ፅ/ቤት የስራና ክህሎት ሚኒስቴር መሬቱን እንዲለቅ በደብዳቤ ቢጠይቅም ሚኒስቴር መስሪያቤቱ ግን በካርታ የተሰጠንን ቦታ ሊለቅልን አልቻለም።ክፍለከተማው ለማስለቀቅ ግብረ ኃይል ቢልክም በተደጋጋሚ በፌደራል ፖሊስ ክልከላ ተደርጓል።ዜጎች በሀገር ውስጥም ይሁን በውጪ ሀገራት የስራ ዕድል እንዲያገኙ ምቹ ሁኔታን የሚፈጥረው ተቋሙ፣ጡረተኞች እና ምንም ገቢ የሌላቸው አሮጊቶች እና አዛውንቶች እንድንገላታ አድርጓል፤የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ካቢኔ የወሰነልንን ውሳኔ እንዳንጠቀም ሚኒስቴር መስሪያቤቱ መብታችንን ነፍጎናል የሚል ቅሬታቸውን ገልፀዋል።
ከ11 ዓመታት በላይ ይዞታቸውን አስረክበው ከቀያቸው ተፈናቅለው በኪራይ ቤት የሚገኙ 63 አባሎቻችን የቤት ባለቤት የመሆን ህልማቸው ጨልሟል።መሬታቸውን ሲያስረክቡ የተቀበሉት ለኪራይ የሚሆን ገንዘብ አልቆባቸው ለከፋ ማህበራዊ ቀውስ ስለተዳረጉ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር አፋጣኝ ምላሽ ይስጠኝ፣ስራና ክህሎት ሚኒስቴርም የተፈቀደልንን ቦታ በአስቸኳይ ይልቀቅልን ሲሉም አቶ ንጉሴ ቅሬታቸውን አቅርበዋል።
ዲዛይን ወጥቶላቸው አጠቃላይ 100,000 ካ.ሜ የሚገነቡት ሁለት የመኖሪያ እና ኮሜርሻል ህንፃዎች ከመሬት በታች እና መሰረቱን ጨምሮ እያንዳንዳቸው ባለ27 ወለል ናቸው።አጠቃላይ ወጪያቸውም ከ6 እስከ 8 ቢሊዮን ብር የሚገመት ነው።
እንደ አቶ ንጉሴ ገለፃ፣ፕሮጀክቱ እውን ሆኖ ሲጠናቀቅ፣ ስሟን ግብሯ ለሰመሩላት አዲስ አበባ ብሎም እንደአዲስ ለተገነባችው ካዛንቺስ ተጨማሪ ዕድገትና ውበትን ያጎናፅፋል።
የግንባታ ፍቃድ ተሰጥቶን በከፍተኛ ወጪ ዲዛይን አሰርተን፣ኮንትራክተር ቀጥረን፣ትላልቅ የግንባታ መሳሪያዎችን አስገብተን 200 ሚሊዮን ብር ወጪ በማድረግ የቁፋሮ ስራ ብንጀምርም፣ በግንባታ ዲዛይን ላይ ተጠቃሎ የሚገኘውን 970 ካ.ሜ ቦታ ስራና ክህሎት ሚኒስቴር ሊለቅልን ስላልቻለ የግንባታ ስራችንን አስተጓጉሎብናል።ለአላስፈላጊ ወጪ፣ኪሳራ እና እንግልትም ዳርጎናል ሲሉ የኬዲ ሪልስቴት ዴቨሎፐርስ አ.ማ የቦርድ ሰብሳቢው ገልጸዋል።
መንግስትም ቢሆን ቦታው አፅድቶ ባለማስረከቡ
ለተነሺዎች በመደበኛነት ከከፈለው ካሳ በተጨማሪ ለኪሳራ ተዳርጎ 10 ሚሊዮን ብር ለሪልስቴቱ መክፈሉን ያስረዱት የቦርድ ሰብሳቢው፣አሁንም ቢሆን ለአምስት ዓመታት ያህል መሬቱን ያልተረከብንበትን ተጨማሪ ካሳ ሊሰጠን ይገባል ብለዋል።

4 months ago