Logo
FastMereja
የኢትዮ ኢንጂነሪንግ ግሩፕ የነዳጅ ቁጠባ ስትራቴጂን ይፋ አደረገ

​#fastmereja I የኢትዮ ኢንጂነሪንግ ግሩፕ በዓለም አቀፍ እና በሀገር አቀፍ ደረጃ የተከሰተውን የነዳጅ አቅርቦት እጥረት ለመቋቋም የሚያስችሉ አዳዲስ የቁጠባ መመሪያዎችን መተግበር መጀመሩን አስታወቀ። ተቋሙ የምርት ሂደቱን ሳይነካ የነዳጅ ፍጆታን ለመቀነስ የወሰናቸው እርምጃዎች ውጤታማ መሆናቸውን የገለጸ ሲሆን፣ በአንዳንድ መገናኛ ብዙኃን "ሰራተኞች ወደ ስራ እንዳይገቡ ተደረገ" ተብሎ የተሰራጨው መረጃ ግን መሰረተ ቢስ መሆኑን አረጋግጧል።

​ከ3 ሺህ በላይ ሰራተኞችን የሚያስተዳድረው ይህ ግዙፍ የመንግስት የልማት ድርጅት፣ ወቅታዊውን ቀውስ ለመወጣት ካከናወናቸው ዋና ዋና ተግባራት መካከል በአካል ተገኝቶ የሚደረጉ ስብሰባዎችን በማስቀረት በቨርቹዋል (Zoom) እንዲካሄዱ ተደርጓል።

​የሰራተኞች ትራንስፖርት ስምሪት በቅንጅት እንዲፈጸም በማድረግ የተሰማሩ ተሽከርካሪዎች ቁጥር ቀንሷል። የስራ መሪዎች ወርሃዊ የነዳጅ አበል እንዲቀነስ ተወስኗል። ከልዩ ተልዕኮ ውጭ ተሽከርካሪዎች ከስራ ሰዓት ውጭ እንዳይንቀሳቀሱ ታግደዋል።

​ተቋሙ በሰጠው መግለጫ፣ ሰራተኞች ተገደው ፈቃድ እንዲወጡ ተደርጓል የሚለው ዘገባ ከእውነት የራቀ መሆኑን ጠቅሶ፣ ሰራተኛው እንደተለመደው የድርጅቱን ሰርቪስ ተጠቅሞ ወደ ስራ ገበታው እየገባ መሆኑን አስታውቋል።

2 months ago

No replys yet!

Be the first to share what you think — your comment will appear here.