Logo
SeledaPost
የኢትዮጵያ መድኃኒት አቅራቢ አገልግሎት የጥራት ችግር ያለበትን ፌኒቶይን (Phenytoin) መድኃኒት በአስቸኳይ እንዲመለስ አዘዘ።

የኢትዮጵያ መድኃኒት አቅራቢ አገልግሎት የባህር ዳር ቅርንጫፍ፣ ሜዲካመን ባዮቴክ ሊሚትድ (Medicamen Biotech limited) በተባለ ኩባንያ የተመረተ የፌኒቶይን 100 ሚሊ ግራም (Phenytoin 100 mg) ታብሌት መድኃኒት የጥራት ችግር ስላለበት ከጤና ተቋማት በአስቸኳይ እንዲሰበሰብ ትዕዛዝ አስተላልፏል።

ቅርንጫፍ መሥሪያ ቤቱ ለሁሉም የጤና ተቋማት በጻፈው ደብዳቤ ላይ እንደገለጸው፣ በአምራቹ የተመረቱት የዚህ መድኃኒት ባቾች (batches) በሙሉ የጥራት ጉድለት የታየባቸው በመሆኑ ተመላሽ እንዲያደርጉ ማሳሰቢያ ሰጥቷል።

ይሁን እንጂ እስካሁን ድረስ አንዳንድ የጤና ተቋማት መድኃኒቱን የመለሱ ቢሆንም፣ አንዳንድ ተቋማት ግን እስካሁን አለመመለሳቸውን አገልግሎቱ ገልጿል።

በመሆኑም መድኃኒቱን ያልመለሱ ተቋማት ያላቸውን ቀሪ መጠን በደብዳቤ ገልጸው እስከ ትላንት ሐምሌ 18 ቀን 2018 ዓ.ም ድረስ እንዲያሳውቁ ጥብቅ ማሳሰቢያ ሰጥቷል።

የመድኃኒት አቅርቦት አገልግሎቱ አክሎም፣ ይህንን ትዕዛዝ ተላልፈው መድኃኒቱን ተመላሽ የማያደርጉ ተቋማት ሙሉ ኃላፊነቱን እንደሚወስዱ አስጠንቅቋል።

ቲክቫህ ኢትዮጵያ ከመድኃኒት አቅራቢ አገልግሎት እንዳረጋገጠው በተጠቀሰው ባች የተመረተው ምርት የጥራት ችግር ያለበት በመሆኑ ከ 19 ኙም የመድኃኒት አቅራቢ አገልግሎት ቅርንጫፍ ጽ/ቤቶች እንዲሰበሰቡ ትዕዛዝ መተላለፉን አረጋግጧል።

የፌኒቶይን (Phenytoin) መድኃኒት አብዛኛውን ጊዜ የሚጥል በሽታን (Epilepsy) ለመቆጣጠርና የሚያገለግል መሆኑ ይታወቃል።via tikvah

seledadotio
seledadotio
4 months ago

No replys yet!

Be the first to share what you think — your comment will appear here.