“ንጉሥ አንፈልግም” — በአሜሪካ ታሪክ ታይቶ የማይታወቅ ግዙፍ የሕዝብ ተቃውሞ በፕሬዝዳንት ትራምፕ ላይ ተቀጣጠለ
የኔታ ሚዲያ
ቅዳሜ ዕለት በመላው ዩናይትድ ስቴትስ የሚገኙ ዋና ዋና ከተሞች እና ትናንሽ መንደሮች በሰው ባህር ተጥለቅልቀው ውለዋል። “No Kings” (ንጉሥ አንፈልግም) በሚል መሪ ቃል የተጠራውና በፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ አስተዳደር ላይ ያነጣጠረው ይህ ተቃውሞ በአሜሪካ የፖለቲካ ታሪክ ውስጥ እጅግ ከፍተኛ ቁጥር ያለው ሕዝብ የተሳተፈበት ኩነት ሆኖ ተመዝግቧል።
የተቃውሞው መንስኤ እና መነሻ
ሰልፈኞቹ አደባባይ የወጡት ፕሬዝዳንት ትራምፕ ሕገ-መንግስታዊ ገደቦችን በመጣስ እንደ “ንጉሥ” ያለ ገደብ የሌለው ስልጣን ለመጠቀም እየሞከሩ ነው በሚል ስጋት ነው።
በተለይም፦
* በኢራን ላይ እየተደረገ ያለው የጦርነት ዛቻ
* የፌዴራል ወኪሎች (ICE) በከተሞች ውስጥ የሚያደርጉት ጠንካራ የኢሚግሬሽን ህግ ማስከበር እርምጃ፣
* እና በወኪሎቹ እጅ የተገደሉ ሞት ተከትሎ የመጣ ቁጣ ለሰልፉ መነሻ ሆነዋል።
የጥንካሬ ማሳያ የተቃውሞው ዋነኛ ማዕከል የነበረችው በሚኒሶታ ግዛት የምትገኘው የቅዱስ ጳውሎስ (St. Paul) ከተማ ነበረች።
በሺዎች የሚቆጠሩ ሰልፈኞች የኢሚግሬሽን ወኪሎችን ወረራ በመቃወም ትከሻ ለትከሻ ተደጋግፈው ቆመዋል። ታዋቂው ድምፃዊ ብሩስ ስፕሪንግስተን በቦታው ተገኝቶ ባደረገው ንግግር፦ “ይህ ወደ ኋላ የሚመልስ ቅዠት እና በአሜሪካ ከተሞች ላይ የሚደረገው ወረራ በፍጹም ተቀባይነት የለውም አሁንም አሜሪካ መሆናችንን አሳይታችኋል” ሲል ለሰልፈኞቹ አድናቆቱን ገልጿል።
ከኒው ዮርክ እስከ አይዳሆ
ተቃውሞው በዲሞክራቶች ምሽግ በሆነችው ኒው ዮርክ ሲቲ ብቻ ሳይወሰን፣ ትራምፕ በ2024 ምርጫ 66% ድምፅ ባገኙባት የአይዳሆ ግዛት ጭምር ተስተውሏል።
አዘጋጆቹ እንደሚሉት ከሆነ በሰልፉ ላይ ለመሳተፍ ከ9 ሚሊዮን በላይ ሰዎች አቅደው የነበረ ሲሆን በመላው አሜሪካ ከ3,100 በላይ ኩነቶች ተመዝግበው ተካሂደዋል።
አብዛኞቹ ሰልፎች ሰላማዊ በሆነ መንገድ ቢጠናቀቁም በአንዳንድ ከተሞች ግን ግጭቶች ተፈጥረዋል።
* በሎስ አንጀለስ፦ ፖሊስ በፌዴራል እስር ቤት አቅራቢያ የተሰበሰቡትን ለመበተን አስለቃሽ ጭስ ተጠቅሟል።
* በዴንቨር፦ መንገድ የዘጉ ተቃዋሚዎች ላይ የጢስ ቦምብ የተወረወረ ሲሆን፣ ተቃዋሚዎችም መልሰው በመወርወር ምላሽ ሰጥተዋል። በዚህም ሳቢያ ቢያንስ ዘጠኝ ሰዎች በቁጥጥር ስር ውለዋል።
ይህ “No Kings” የተሰኘው እንቅስቃሴ ከጊዜ ወደ ጊዜ እየጠነከረ የመጣ ሲሆን በፕሬዝዳንት ትራምፕ አስተዳደር እና በተቃዋሚዎቻቸው መካከል ያለው ልዩነት ከመቼውም ጊዜ በላይ መስፋቱን አመላካች ሆኗል።
የሰልፉ አስተባባሪዎች ትራምፕ አካሄዳቸውን ካልቀየሩ ተቃውሞው ተጠናክሮ እንደሚቀጥል ዝተዋል።

3 months ago