Logo
FIDEL POST NEWS
የፊንቴክ ኢንቨስትመንት ሥራ አስኪያጅ በከባድ የማታለል ወንጀል ተከሰሰ

​በአዲስ አበባ የፊንቴክ ኢንቨስትመንት ሥራ አስኪያጅ የሆኑት ዳንኤል ዮሐንስ፣ ከ600 ሚሊዮን ብር በላይ በማጭበርበር ወንጀል ክስ ተመሰረተባቸው።

ዐቃቤ ሕግ እንደገለጸው፣ ተከሳሹ "ሄሎ ታክሲ" እና "ፊንቴክ ኢንቨስትመንት" የተባሉ ድርጅቶችን በመጠቀም፣ የኤሌክትሪክ ተሽከርካሪዎችን በዱቤ እናስረክባለን የሚል አሳሳች ማስታወቂያ በታዋቂ ግለሰቦች እና ማህበራዊ ሚዲያዎች አስነግረዋል።

​ተከሳሹ ከ5 ሺህ በላይ ተመዝጋቢዎችን ለቅድመ ክፍያ እና ለምዝገባ በሚል ከፍተኛ ገንዘብ እንዲከፍሉ ካደረጉ በኋላ፣ መኪኖቹን ሳያስረክቡ ድርጅቱን ዘግተው መሰወራቸው በክሱ ተመልክቷል።

ድርጊቱ የ1996 ዓ.ም የወንጀል ሕግን እና የኮምፒውተር ወንጀል አዋጅን የጣሰ መሆኑ ተገልጿል።

​በተጨማሪም፣ ተከሳሹ ቀደም ሲል በኢንተርፖል ከተያዘ ግብረ-አበር ጋር በመሆን፣ የውሸት ርክክብ ቪዲዮዎችን በማሳየት እና "መኪናዎች በመጓጓዝ ላይ ናቸው" የሚል ሀሰተኛ መረጃ በማሰራጨት 19 ተደራራቢ ወንጀሎችን መፈጸማቸው ተጠቅሷል።

ጉዳዩን የፌዴራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት ልደታ ምድብ 2ኛ ልዩ ልዩ ወንጀል ችሎት እየተመለከተው ይገኛል።

ምንጭ: FMC
2 months ago

No replys yet!

Be the first to share what you think — your comment will appear here.