Logo
Getu Temesgen
ዶናልድ ትራምፕ የኢራን ''መሪ'' እንዲሆኑ መጠየቃቸውን ተናገሩ
#ethiopia | ​የአሜሪካው ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ ባደረጉት ንግግር፣ የኢራን ባለስልጣናት የሀገሪቱ "መንፈሳዊ መሪ" እንድሆን ጠይቀውኛል ሲሉ በድፍረት ተናገሩ።

ትራምፕ ጥያቄውን "አመሰግናለሁ ግን አልፈልገውም" በማለት ውድቅ ማድረጋቸውን ገልጸዋል።

​እንደ ትራምፕ ገለጻ፣ የኢራን መሪዎች ከአሜሪካ ጋር ስምምነት ለማድረግ ቢፈልጉም የገዛ ህዝባቸውንና የአሜሪካን ጥቃት በመፍራት በይፋ ለመናገር ተቸግረዋል ብለዋል።

ይሁን እንጂ የኢራን ወገን ከዋሽንግተን ጋር ድርድር እያደረግን አይደለም በማለት የትራምፕን ንግግር አስተባብለዋል።

​ይህ በእንዲህ እንዳለ፣ አሜሪካ ወደ መካከለኛው ምስራቅ ተጨማሪ ወታደሮችን ለመላክ እያሰበች መሆኑንና በትራምፕ አስተዳደር ውስጥ በጉዳዩ ላይ ከፍተኛ ክርክር መኖሩ አየተነገረ ይገኛል።

Getu Temesgen - (ጌጡ ተመስገን)
#getutemesgen #getu #ጌጡ #fidelpost

7 months ago

No replys yet!

Be the first to share what you think — your comment will appear here.