በ48.8 ሚሊዮን የአሜሪካን ዶላር ወጪ 500 ሺህ ዘመናዊ ቆጣሪዎችን ለመግጠም እየተሰራ ነው
የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት በ48.8 ሚሊዮን የአሜሪካን ዶላር ወጪ በሀገር አቀፍ ደረጃ 500 ሺህ ስማርት የቅድመ ክፍያ ቆጣሪዎችን ለነባርና አዲስ ደንበኞቹ ለመግጠም የሚያስችል ፕሮጀክት እየተገበረ ነው፡፡
በፕሮጀክቱ 125 ሺህ ስማርት ሶስት ፌዝ፣ 25 ሺህ ስማርት ነጠላ ፌዝ እንዲሁም 350 ሺህ ኦፍላይን (Semi-Smart) ነጠላ ፌዝ በድምሩ 500 ሺህ ዘመናዊ የቅድመ ክፍያ ቆጣሪዎችን ለመግጠም ታቅዶ እየተሰራ ይገኛል፡፡
እስካሁን በተከናወነው ሥራ 60 ሺህ 457 ነጠላ ፌዝ ቆጣሪዎችን እስከ 7.5 ኪሎ ዋት ድረስ ኃይል ለሚጠቀሙ ለመኖሪያና ለንግድ ደንበኞች ተገጥመዋል፡፡
በተጨማሪም 7 ሺህ 13 ባለ ሦስት ፌዝ ቆጣሪዎች ከ8 እስከ 24 ኪሎ ዋት ድረስ ኃይል ለሚጠቀሙ ለመኖሪያ፣ ለንግድና ለአነስተኛ ኢንደስትሪዎች ተገጥመው አገልግሎት እየሰጡ ይገኛሉ፡፡
እነዚህ ዘመናዊ ቆጣሪዎች የቅድመ ክፍያ ደንበኞች ወደ አገልግሎት መስጫ ማዕከላት ሳይሄዱ የእጅ ስልካቸውን በመጠቀም ቶክን ቁጥር በመግዛት የኤሌክትሪክ ኃይል እንዲሞሉ የሚያስችሉ ናቸው፡፡
ፕሮጀክቱ በአሁን ወቅት ከ67 ሺህ በላይ ደንበኞች በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ፣ በኢትዮ ቴሌኮምና በአዋሽ ባንክ የሞባይል አፕሊኬሽኖች በሳምንት ሰባቱንም ቀናት 24 ሰዓት የትም መሄድ ሳይጠበቅባቸው ቤታቸው ሆነው የኤሌክትሪክ ኃይል መግዛት እንዲችሉ ዕድል ፈጥሯል፡፡
ይህ ፕሮጀክት ቀድሞ የነበሩ ለአብነት የቅድመ ክፍያ ካርድ መጥፋት፣ የካርድ መበላሸት፣ የኔትወርክ መቆራረጥ እንዲሁም ቆጣሪው ላይ ብር አልገባልኝም የሚሉትን ችግሮች ያስቀራል፡፡
በተጨማሪም ከፍተኛ በሆነ ኃይል መጨመር (Over voltage) ምክንያት የሚመጣን የንብረት መቃጠል ይከላከላል፣ ደንበኞች በሚሰጣቸው መሳሪያ አማካኝነት (Customer Interface Unite) ፍጆታቸውን መከታተል በመቻላቸው አጠቃቀማቸውን መቆጠብ እና ወጪ እንዲቀንሱ ያስችላቸዋል፡፡
#የኢትዮጵያኤሌክትሪክአገልግሎት

4 months ago