በኩዌት የኑክሌር ስጋት ማስጠንቀቂያ ተሰጠ
በመካከለኛው ምስራቅ እየተባባሰ የመጣውን ቀውስ ተከትሎ፣ የኩዌት መንግስት ሊኖር ስለሚችል የኑክሌር ጨረር ስርጭት ለዜጎቹ አስቸኳይ ማስጠንቀቂያ አስተላልፏል።
ባለስልጣናቱ ህዝቡ ምንም አይነት ድንጋጤ ውስጥ ሳይገባ በቤቱ እንዲቆይ አሳስበዋል። በቤት ውስጥ በሚቆዩበት ወቅትም ማንኛውንም የውጭ አየር ወደ ውስጥ እንዳይገባ መስኮቶችንና በሮችን በጥንቃቄ እንዲዘጉ መመሪያ ተሰጥቷል።
ይህ እርምጃ የተወሰደው በጎረቤት ሀገር ኢራን የሚገኘው የቡሸር የኑክሌር ጣቢያ ጥቃት እንደደረሰበት የሚገልጹ ዘገባዎች ከወጡ በኋላ ለጥንቃቄ ሲባል እንደሆነ ታውቋል።
የኩዌት የሀገር ውስጥ ጉዳይ ሚኒስቴር አዲሱን የብሔራዊ የአደጋ ጊዜ ማስጠንቀቂያ ስርዓት በመጠቀም መረጃው ለሁሉም ነዋሪዎች እንዲደርስ እያደረገ ይገኛል።
ምንጭ፦ የኩዌት ብሔራዊ የዜና አገልግሎት (KUNA)

2 months ago