የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ በአዲስ አበባ እምብርት ዘመናዊ ዋና መሥሪያ ቤት ሊያስገነባ ነው
#ethiopia | የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ እያደገ የመጣውንና እየተወሳሰበ ያለውን የፋይናንስ ሥርዓት በብቃት ለመምራት የሚያስችለው አዲስና ዘመናዊ ዋና መሥሪያ ቤት ሊያስገነባ መሆኑን አስታወቀ።
ባንኩ አሁን ዋና መሥሪያ ቤቱ በሚገኝበትና የፋይናንስ ማዕከል ተብሎ በሚጠራው ብሔራዊ ቴአትር አካባቢ፣ ከግማሽ ሄክታር በላይ በሆነ ቦታ ላይ ይህንን ግዙፍ ሕንፃ ለማሳረፍ አቅዷል።
የአዲሱ ሕንፃ ዋና ዋና ገጽታዎች፦
* የቦታ ስፋት፦ ሕንፃው በ5,700 ካሬ ሜትር ቦታ ላይ የሚያርፍ ይሆናል።
* ዘመናዊ አገልግሎቶች፦ በውስጡ ሰፊ የስብሰባ እና የማሠልጠኛ ማዕከላት፣ የተደራጀ የአይቲ ማዕከል፣ ዘመናዊ የመኪና ማቆሚያ እና ሌሎች ተያያዥ አገልግሎቶችን ያካትታል።
* የዲዛይን ዝግጅት፦ ባንኩ ለሕንፃው የሚመጥን የላቀ ንድፍ (Design) እንዲሠራለት ለአማካሪ ድርጅቶች ጥሪ አቅርቧል።
ብሔራዊ ባንክ በአዲስ አበባ ከሚገነባው ዋና መሥሪያ ቤት በተጨማሪ፣ በተመረጡ አራት የሀገሪቱ ከተሞች የቅርንጫፍ ሕንፃዎችን ግንባታ እያከናወነ ይገኛል። ከእነዚህም መካከል በድሬዳዋ እና በሐዋሳ ከተሞች እየተገነቡ ያሉት ሕንፃዎች ይጠቀሳሉ።
ይህ አዲስ ግንባታ የሀገሪቱን የፋይናንስ ዘርፍ ወደ ተሻለ የቴክኖሎጂ እና የአሠራር ምዕራፍ ለማሸጋገር የሚደረገው ጥረት አካል እንደሆነ ተገልጿል ያለው ቅዳሜ ገበያ ነው
Getu Temesgen - (ጌጡ ተመስገን)
#getutemesgen #getu #ጌጡ #ethiopia #nbe #nationalbank #addisababa #financecenter #construction #economynews

2 months ago