ትራምፕ፡ "የደወሉት ኢራኖች ናቸው፤ እኔ አይደለሁም"
ዶናልድ ትራምፕ ከአሜሪካ ጋር እየተደረገ ስላለው ድርድር "የደወሉት ኢራኖች እንጂ እኔ አይደለሁም" ሲሉ ተናግረዋል።
ቴህራን ንግግር እያደረግን አይደለም በማለት ብታስተባብልም፣ ትራምፕ ግን ከኢራን "ከፍተኛ አመራሮች" ጋር እስከ እሁድ ምሽት ድርድር ሲካሄድ እንደነበር ገልጸዋል።
በዚህ ንግግር ውስጥ የ15 ነጥብ ስምምነት ላይ ለመድረስ ጥረት እየተደረገ መሆኑንና ኢራን የኑክሌር መሣሪያ ላለመያዝ መስማማቷን ጠቁመዋል።
ይሁን እንጂ ትራምፕ "ስምምነት ላይ ለመድረስ ዋስትና መስጠት አልችልም" ሲሉ ጥንቃቄ የታከለበት አስተያየት ሰጥተዋል።
በሌላ በኩል የኢራን ባለሥልጣናት የትራምፕ ንግግር "የገበያ ዋጋን ለመቆጣጠር የታለመ የሐሰት ዜና ነው" ሲሉ ነቅፈውታል።
ምንጭ: ፎክስ ኒውስ

2 months ago