በሚታጠቡበት ወቅት ቅድሚያ ሊሰጠው የሚገባው የሰውነት ክፍል የትኛው ነው?
ገላን የመታጠብ ልማድ አብዛኞቻችን በየቀኑ የምናከናውነው ተግባር ቢሆንም፣ አስተጣጠባችን ግን በቆዳችን ንጽህና ላይ ትልቅ ልዩነት እንደሚያመጣ የዘርፉ ባለሙያዎች ይናገራሉ።
ቀዳሚው የታጠቢያ ክፍል፦ ጸጉር
የቆዳ ስፔሻሊስቶች እንደሚሉት ከሆነ፣ ገላን በሚታጠቡበት ወቅት ሁልጊዜም ቅድሚያ መሰጠት ያለበት ለጸጉር (ለራስ ቅል) ነው።
ምክንያቱ፦
ጸጉርዎን በሚታጠቡበት ወቅት የሻምፑ፣ የኮንዲሽነር፣ የቅባት እና የቆሻሻ ቅሪቶች በሰውነትዎ ላይ ይወርዳሉ።
ጸጉርዎን መጨረሻ ላይ የሚታጠቡ ከሆነ፣ እነዚህ ኬሚካሎች እና ቆሻሻዎች አስቀድመው ባጠቡት ንጹህ ቆዳ ላይ ሊቀሩና ለቆዳ መቆጣት ወይም ለቆሻሻ መከማቸት ምክንያት ሊሆኑ ይችላሉ። ስለዚህ ጸጉርን ቀድሞ መታጠብ ቆሻሻ ወደ ሌላ የሰውነት ክፍል እንዳይሰራጭ ይረዳል።
ከጸጉር ቀጥሎ ያለው ቅደም ተከተል
ባለሙያዎች ከራስ ቅል በመጀመር ወደ ታች የሚወርድ (አጠባበቅን ይመክራሉ፦
👉ጸጉር እና የራስ ቅል
👉ፊት፣ አንገት እና ደረት
👉ብብት፣ እምብርት እና ጭን አካባቢ (ባክቴሪያ የሚከማችባቸው ቦታዎች ስለሆኑ ልዩ ትኩረት ይሻሉ)
👉እግር
ተጨማሪ የባለሙያ ምክሮች
የውሃ ሙቀት፦ በጣም ሙቅ ውሃ መጠቀም የቆዳን ተፈጥሯዊ እርጥበት ስለሚያጠፋ፣ ለብ ያለ ውሃ መጠቀም ይመከራል።
የቆዳ ፒኤች (pH)፦ የቆዳን ተፈጥሯዊ ሚዛን የሚጠብቁ ሳሙናዎችን ይጠቀሙ።
ማድረቅ፦ ከታጠቡ በኋላ ሰውነትን በተለይም ጸጉርን በሚገባ ማድረቅ ያስፈልጋል። እርጥበት መቆየት ለፈንገስ እና ለባክቴሪያ መራባት ምቹ ሁኔታ ይፈጥራል።
ምንጭ፦ በLeidy Puente የቀረበ የጤና ዘገባ

3 months ago