ኢትዮጵያዊ የሚዲያ ተቋም አለም አቀፍ ሽልማት አሸነፈ
#ethiopia |በደቡብ አፍሪካ ጆንሀንስበርግ በተካሄደው የ2026 SABRE ሽልማት
ስፖትላይት ኮሚኒኬሽን እና ማርኬቲንግ አሸናፊ ሆኗል።
ይህ ሽልማት ኢትዮጵያ በሀገራዊ የሽልማት ውድድር ላይ ስታሸንፍ የመጀመሪያው በመሆኑ፣ ለሀገሪቱ የፈጠራ እና የኮሚኒኬሽን ዘርፍ ታሪካዊ ምዕራፍ ነው::
ተቋሙ በዓለም አቀፍ ደረጃ ምርጥ የህዝብ ግንኙነት (PR) ስራዎችን ለመመዘን የሚሰጠውን እና የዓለማችን ትልቅ የሽልማት መርሃ-ግብር የሆነውን የ2026 SABRE ሽልማትን ነው ማሸነፍ የቻለው::
ስፖትላይት ኮሚኒኬሽን እና ማርኬቲንግ በ2026 SABRE ሽልማት በምስራቅ አፍሪካ ምርጥ ኤጀንሲ በመባል በይፋ አሸናፊ ሆኗል::
ይህ ታዋቂ ሽልማት መጋቢት 8 ቀን በደቡብ አፍሪካ ጆሃንስበርግ ‘ዘ ኬንት ማልሮዝ አርክ’ በተካሄደ ደማቅ የሽልማት ስነ-ስርዓት ላይ ተበርክቷል::
ሽልማቱ ለስፖትላይት ኮሚኒኬሽን እና ማርኬቲንግ የተበረከተለት ለሳፋሪኮም ኢትዮጵያ በሰራው አዲስና ፈጠራ የታከለበት የዘመቻ ስራ ነው::
በብራንዲንግ፣ በስም ዝና እና በተሳትፎ ዘርፍ የላቀ ውጤትን የሚመዝነው SABRE ሽልማት በዓለም አቀፍ ደረጃ በህዝብ ግንኙነት ዘርፍ ትልቁ የሽልማት ውድድር ነው::
በዘንድሮው የአፍሪካ ደረጃ ውድድር ላይ ከ500 በላይ ስራዎች የቀረቡ ሲሆን፣ ስፖትላይት ኮሚኒኬሽን እና ማርኬቲንግ ስራው 120 ኤጀንሲዎች ካለፉበት ጠንካራ ስራዎች ዝርዝር ውስጥ ቀዳሚ በመሆን አሸንፏል::
ስፖትላይት ኮሚኒኬሽን እና ማርኬቲንግ የኢትዮጵያ የህዝብ ግንኙነት ኤጀንሲዎች በአህጉራዊ መድረኮች ላይ ተሳታፊ ብቻ ሳይሆኑ በስትራቴጂካዊ ልህቀትም መሪ መሆናቸውን ያስመሰከረ ነው::
ይህ ሽልማት ለስፖትላይት ለተለመደው የአገልግሎት አሰጣጥ ዘዴው መጥቶ፣ ከዓለም አቀፍ ኩባንያዎች፣ መንግስታዊ ካልሆኑ ተቋማት እና ታላቅ ራዕይ ካላቸው አጋሮች ጋር በመሆን ተደራሽነታቸውን የሚያሰፉበት እና ዘላቂ ተጽዕኖ የሚፈጥሩበት ስልታዊ የእድገት መድረክ መሆኑን ያረጋገጠ ነው ተብሏል::
አስቸጋሪ በሆነው የውድድር ገበያ ውስጥ፣ ስፖትላይት ኮሚኒኬሽን እና ማርኬቲንግ ተቋማት ዓላማቸውን ያሳኩ ዘንድ የሚያስፈልጋቸውን ሙያዊ ድጋፍ እና መሠረት ልማት እንደሚያቀርብ ተገልጿል::
ይህ ሽልማት በሀገሪቱ እያደገ ላለው የሚዲያ እና የማርኬቲንግ ዘርፍ ዓለም አቀፍ እውቅናን ያጎናጸፈ ነው::
ስፖትላይት የሀገር ውስጥ ተጫዋቾች ከሀገር አልፎ ተጽዕኖ መፍጠር የሚችሉ ዓለም አቀፍ ደረጃቸውን የጠበቁ ስራዎችን መስራት እንደሚቻል በተግባር ማሳየቱን ነው የተገለፀው።
ጌጡ ተመስገን (Getu Temesgen
#getutemesgen #spotlightcommunications #sabreawards #publicrelations #marketingsuccess #ethiopia #eastafrica #safaricomethiopia #awardwinner

3 months ago