Logo
Getu Temesgen
"አካልን በብቃት" የተሰኘ መፅሐፍ ሊመረቅ ነው
#ethiopia | የኢንስትራክተር ዳዊት መኮንን "አካልን በብቃት" የተሰኘ“ 3ኛተኛው መፅሃፍ ሊመረቅ እንደሆነ በተሰጠው ጋዜጣዊ መግለጫ ተነግሯል።

ኢንሰትራክተር ዳዊት ከዚህ ቀደም በሀገራችን ሁሉም አይነት የአካል ብቃት ስልጠና እና የሥነ-ምግብ መመሪያዎችን ባጣመረ መልኩ ለበርካታ ዜጎች ስልጠናዎችን በመስጠት የሚታወቅ ሲሆን እነዚህን ስልጠና እና መመሪያዎች ማንኛውም የሕብረተሰብ ክፍል የትኛውም ስፖርት ቤት መሄድ ሳያስፈልጋቸው ባሉበትና በተመቻቸው ስፍራ በመሆን መስራት እንዲችሉ የሚያስችል መጽሐፍቶችን በማዘጋጀት ይታወቃል፡፡

ለመጥቀስም ያህል የስፖርት ማሽን አጠቃቀም›› በሚል ርዕስ የመጀመሪያ መጽሐፉን ያሳተመ ሲሆን ሁለተኛ መጽሐፉን ደግሞ ‹ስፖርት ያለ መሳሪያ›› በሚል ርዕስ በማሳተም ለአንባቢያን አቅርቧል፡፡

ከዚህም ጋር በተያያዘ ሦስተኛው እና በአመራር ሃላፊነት ያሉ ሰዎች፣በኢንቨስትመንት ሥራ ላይ የተሰማሩ ግለሰቦች፣ በርካታ የኪነ-ጥበብ ባለሙያዎችና ተጽዕኖ ፈጣሪ ግለሰቦች የተሳተፉበትን ‹‹አካል በብቃት››የተሰኘ መጽሐፍ አዘጋጅቶ ሐሙስ መጋቢት 24 ቀን 2018ዓ.ም ከቀኑ 10:00 ሰዓት ጀምሮ ለማስመረቅ መንገድ ላይ መሆኑን በተሰጠዉ ጋዜጣዊ መግለጫ አዉቀናል።

መፅሃፍ በአስራ አንድ ምዕራፎች የተሰናዳ ሲሆን ከነዚህ ምእራፎች ውስጥ የህፃናት ፊትንስ ምን ይመስላልሰነ ምግብ ምን መምሰል አለበት?

ባህላዊ ጭፈራ ከስፖርቱ ጋር ያለዉ ሳይንሳዊ ይዘት ምን ይመስላል የሚሉትን እና ሌሎች ምእራፎችን ይዟል።

መፅሃፉ በ250 ገፆች ተቀንብቦ በበርካታ መፅሄቶች እና ህትመት ስራዎች የረጅም ግዜ ልምድ ያካበተው ለታሪክ አድቨርታይዚንግ እና ህትመት ለህትመት አብቅቶታል።

መፅሀፉን በ1199 ብር ለንባብ ቀርቧል።
#getutemesgen #getu #ጌጡተመስገን

7 months ago

No replys yet!

Be the first to share what you think — your comment will appear here.