የሲድኒ ስዊኒ ሃብት በሁለት ዓመት ውስጥ በ30 ሚሊዮን ዶላር አደገ
ታዋቂዋ አሜሪካዊት ተዋናይ ሲድኒ ስዊኒ በሁለት ዓመታት ውስጥ ብቻ የሀብት መጠኗን በ30 ሚሊዮን ዶላር ማሳደጓ ተገለጸ።
የ28 ዓመቷ ተዋናይት አጠቃላይ የሀብት መጠን ከ10 ሚሊዮን ዶላር ተነስቶ በአሁኑ ወቅት 40 ሚሊዮን ዶላር መድረሱን ዴይሊ ሜይል ዘግቧል።
ለዚህ ከፍተኛ የገቢ ዕድገት ምክንያት የሆኑት "Anyone But You" እና "The Housemaid" የተሰኙ ስኬታማ ፊልሞች እንዲሁም ከአሜሪካን ኢግል እና መሰል ዓለም አቀፍ ብራንዶች ጋር ያደረገቻቸው የማስታወቂያ ውሎች ናቸው። በተጨማሪም "Syrn" የተሰኘ የውስጥ ልብስ ብራንድ በራሷ ስም መጀመሯ ለገቢዋ መጨመር ትልቅ ድርሻ አበርክቷል።
ተዋናይቷ በቅርቡ በሚለቀቀው "Euphoria" ተከታታይ ድራማ ሶስተኛ ክፍል ላይ ለምታሳየው ተሳትፎም ከፍተኛ ክፍያ እንደምትቀበል ይጠበቃል።

3 months ago