600 ሰው የሚይዘው የኤምሬትስ አውሮፕላን 25 ተሳፋሪዎችን ብቻ ጭኖ በረረ
በቅርቡ የወጣ የብሉምበርግ ዘገባ እንደሚያመለክተው በመካከለኛው ምስራቅ ባለው ጦርነት ምክንያት የኤምሬትስ አየር መንገድ (Emirates) ከፍተኛ የተሳፋሪዎች ቁጥር መቀነስ እያጋጠመው ይገኛል።
በተለይም ከፓሪስ ወደ ዱባይ የተጓዘውና 600 ተሳፋሪዎችን የመያዝ አቅም ያለው ግዙፉ ኤርባስ ኤ380 (Airbus A380) አውሮፕላን የጫነው 25 ተሳፋሪዎችን ብቻ እንደነበር ተገልጿል።
በተመሳሳይ ከኒውዮርክ ወደ ዱባይ የተነሳው በረራም 35 ተሳፋሪዎችን ብቻ ይዞ ተጉዟል።
አየር መንገዱ በአሁኑ ወቅት ወደ 100 በሚጠጉ መዳረሻዎች በረራ እያደረገ ቢሆንም፣ በጦርነቱ ምክንያት የአየር ክልሎች መዘጋትና የተሳፋሪዎች "አለመገኘት" ትልቅ ተግዳሮት ሆኖበታል።
ሆኖም በሆርሙዝ ሰርጥ በኩል ያለው የባህር ትራንስፖርት በመስተጓጎሉ፣ የአየር ጭነት (Cargo) አገልግሎት ለአየር መንገዱ ዋነኛ የገቢ ምንጭ ሆኖ ቀጥሏል።
ምንጭ፦ Bloomberg

5 months ago