Logo
Getu Temesgen
🔴 "ክለቡን ማወቄ ለስኬቴ ሚስጥር ነው" — ማይክል ካሪክ
#ethiopia | የኦልድትራፎርዱ ባለቤት ማንችስተር ዩናይትድ በካሪክ ስር አዲስ መንፈስ እያሳየ ይገኛል። የቀያዮቹ ሰይጣኖች አሰልጣኝ ማይክል ካሪክ ለክለቡ ባላቸው ጥልቅ ፍቅር እና እውቀት ዙሪያ አስተያየታቸውን ሰጥተዋል።
አሰልጣኙ አሁን ላስመዘገቡት ውጤት የክለቡን ማንነት ቀድሞውኑ ጠንቅቆ ማወቁ ትልቅ ድርሻ እንዳለው ሲናገሩ፦

"ክለቡን ማወቄ መቶ ፐርሰንት ጠቅሞኛል፤ ይሄንን መካድ አይቻልም። እዚህ ለረጅም ጊዜ መጫወቴ እና ያካበትኩት ልምድ አሁን ላለሁበት ቦታ እንድበቃ ትልቅ መሰረት ሆኖኛል።"

ማንችስተር ዩናይትድ የካሪክን የልምድ ፍሬ ዛሬ ምሽት በሚያደርገው ጨዋታ ዳግም ለመመልከት ይከጅላል።

🏟️ የዛሬ ጨዋታ መርሃ ግብር
* ተጋጣሚዎች፦ ማንችስተር ዩናይትድ 🆚 በርንማውዝ
* ሰዓት፦ ምሽት 5:00
* ውድድር፦ የእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ
ካሪክ እና ልጆቹ የድል ጉዟቸውን ይቀጥሉ ይሆን? ምሽቱን የምናየው ይሆናል።

Getu Temesgen - (ጌጡ ተመስገን)
#getutemesgen #getu #ጌጡ #manutd #michaelcarrick #premierleague #mufc #ethiopia #footballnews #ማንችስተርዩናይትድ #ማይክልካሪክ

7 months ago

No replys yet!

Be the first to share what you think — your comment will appear here.