የኳታሩ ‘ራስ ላፋን’ የኢነርጂ ማዕከል በሚሳይል ተመታ፤ ከፍተኛ ውድመት ደርሷል
በኳታር የሚገኘውና የአገሪቱ ዋነኛ የኃይል ማምረቻ ማዕከል የሆነው የራስ ላፋን (Ras Laffan) የኢነርጂ ማዕከል ከኢራን በተሰነዘረ ሚሳይል ጥቃት ዛሬ አመሻሹን መመታቱን የኳታር ብሔራዊ የነዳጅ ኩባንያ (QatarEnergy) በይፋ አስታውቋል።
በጥቃቱ ምክንያት በማዕከሉ ላይ ከፍተኛ የንብረት ውድመት የደረሰ ሲሆን፣ የተቀሰቀሰውን እሳት ለመቆጣጠር የአደጋ ጊዜ ሰራተኞች በስፍራው ተሰማርተዋል።
ኩባንያው በማህበራዊ ትስስር ገጾቹ ባወጣው መግለጫ መሠረት፣ ሁሉም ሰራተኞች በደህና ሁኔታ ላይ የሚገኙ ሲሆን እስካሁን በሰው ሕይወት ላይ የደረሰ ጉዳት የለም።
ይህ ጥቃት በመካከለኛው ምስራቅ እየተባባሰ የመጣው ግጭት አካል ሲሆን፣ ሰሞኑን በሳዑዲ ዓረቢያ የነዳጅ መሰረተ ልማቶች ላይም ተመሳሳይ ጥቃቶች ተሰንዝረዋል።
ይህ ክስተት በባህረ ሰላጤው ሀገራት ኢኮኖሚ ላይ ከፍተኛ ስጋት የፈጠረ ሲሆን፣ የነዳጅ ዋጋ ላይም ተፅዕኖ ሊያሳድር እንደሚችል ተገምቷል።
ምንጭ፦ QatarEnergy

5 months ago