በጋሞ ዞን በደረሰ የመሬት መንሸራተት አደጋ ከ18ሺህ በላይ ሰዎች ከመኖሪያቸው ተፈናቅለዋል
በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ጋሞ ዞን ባለፈው ሳምንት ለሁለት ቀናት የጣለውን ከባድ ዝናብ ተከትሎ በጋጮ ባባ፣ ቦንኬና ከምባ ዙሪያ ወረዳዎች በተከሰተው የመሬት መንሸራተት እና የየጎርፍ አደጋ ጉዳት የደረሰባቸውን ወገኖች ለመደገፍና ተመሳሳይ የከፋ አደጋ እንዳይደርስ ለመከላከል ስራዎች እየተሰሩ ይገኛል፡፡
በአደጋው ምክንያት የተጎዱና የጠፉ ወገኖችን የማግኘት እና የሰብአዊ ድጋፍ አቅርቦትን የማስተባበር ሥራው በክልሉ የአደጋ ስጋት ሥራ አመራር ምክር ቤት የሚመራ ሲሆን የተጎዱ ወገኖችን ፈልጎ የማዳን፣ ተጋላጭ ወገኖችን በመለየት ለአደጋ ተጋላጭ ከሆኑ አካባቢዎች የማስወጣት ስራ እየተከናወነ ይገኛል፡፡
በዚሁ መሠረት የተጎዱና የጠፉ ወገኖችን ፈልጎ ለማዳን በተደረገ ርብርብ የ81 ዜጎች አስከሬን ወጥቶ ስርዓተ ቀብር የተፈፀመ ሲሆን ከአደጋው ክስተት በኋላ በአካባቢያቸው ያልተገኙ 44 ስዎችን ለማግኘት ጥረት እየተደረገ ነው፡፡
አደጋው ከደረሰበት ጊዜ ጀምሮ እስከ መጋቢት 7 ቀን 2018 ዓ.ም ድረስ የመኖሪያ ቤታቸው በመፍረሱ የተፈናቀሉ 830 ሰዎችን ጨምሮ በአጠቃላይ 18,571 ስዎች የተፈናቀሉ መሆኑን ብስራት ሬዲዮ ከአደጋ ስጋት አመራር አመራር የደረሰው መረጃ ያመላክታል፡፡
ለነዚህ ወገኖች ድጋፍ ለማድረስ በተደረገው ርብርብ በፌዴራል መንግስት፣በክልል መንግሥት፣ በሌሎች የመንግስት ተቋማት፣ በግል ተቋማት ልዩ ልዩ ቁሳቁሶች ድጋፍ የቀረበ ሲሆን የኢትዮጵያ አደጋ ስጋት ስራ አመራር ኮሚሽን በበኩሉ ባደረገው የስራ እንቅስቃሴ አልሚ ምግብ፣ የመጠለያ ድንኳን፣ መመገቢያ፣ አልባሳት እና የንፅህና ቁሳቁሶች በማቅረብና እንዲሰራጭ ማድረጉን አስታውቋል፡፡
እንዲሁም የጋሞ ዞን የተፈጥሮ የመሬት አቀማመጥ በአብዛኛው ተዳፋታማነት ከ25 ዲግሪ በላይ በመሆኑ በአካባቢው ከባድ ዝናብ ሲዘንብ የመሬት መንሸራተት እና ናዳ ሊያስከትል እንደሚችል በተለያዩ ጥናቶች በመመላከቱ ሰፊ የልማት ስራ የሚያስፈልገው ነው፡፡
በሳምራዊት ስዩም
#ዳጉ_ጆርናል

5 months ago