የዶላር ዋጋ ጭማሪ፦ አንድ ዶላር 157.4654 ብር ደረሰ።"
አዲስ አበባ — መጋቢት 8፣ 2018 ዓ.ም የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ ዛሬ መጋቢት 8 ቀን 2018 ዓ.ም (March 17, 2026) ባካሄደው 21ኛው የውጭ ምንዛሬ ጨረታ፣ የዶላር ዋጋ ካለፉት ቀናት ከፍ ብሎ መዋሉን አስታውቋል።
በዛሬው የጨረታ ውጤት መሰረት፣
የዶላር አማካይ የመሸጫ ዋጋ 157.46 ብር ደርሷል።
1. ለገበያ የቀረበው መጠን 70 ሚሊዮን ዶላር
2. የቀረበው አጠቃላይ የፍላጎት መጠን 241.52 ሚሊዮን ዶላር (ይህም ፍላጎቱ ከአቅርቦቱ እጅግ የላቀ መሆኑን ያሳያል)
3. ከፍተኛው የማሸነፊያ ዋጋ፦ 158.5000 ብር
4. ዝቅተኛው የማሸነፊያ ዋጋ፦ 154.5000 ብር
5. አማካይ የማሸነፊያ ዋጋ፦ 157.4654 ብር
6. የመቁረጫ ዋጋ (Marginal Rate)፦ 157.0183 ብር ሆኗል::
በዚህ ጨረታ ላይ በአጠቃላይ 30 የንግድ ባንኮች የተሳተፉ ሲሆን፣ ካቀረቡት የዋጋ ተወዳዳሪነት አንጻር 9 ባንኮች ብቻ የቀረበውን የውጭ ምንዛሬ ማሸነፍ ችለዋል።
ባለፉት ጥቂት ሳምንታት የዶላር ዋጋ በየጨረታው እያሳየ የመጣው ጭማሪ፣ በገበያው ላይ ያለው የውጭ ምንዛሬ ፍላጎት አሁንም ከፍተኛ መሆኑን ይጠቁማል።
ይህም በቀጣይ ቀናት በሸቀጦች ዋጋ ላይ የራሱ የሆነ ተፅዕኖ ሊኖረው እንደሚችል የኢኮኖሚ ባለሙያዎች ይገምታሉ።
ምንጭ፦ የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ (NBE)
seledadotio

5 months ago