የአፍንጫ ጸጉርን መንቀል ለሞት ሊዳርግ ይችላል? በፊታችን ላይ የሚገኘው "አደገኛው ሶስት ማዕዘን" ሚስጥር!
ብዙዎቻችን ለውበት ሲባል የአፍንጫ ጸጉርን የመንቀል ልምድ ቢኖረንም፣ ይህ ድርጊት አልፎ አልፎ ለከፍተኛ የጤና እክል አልፎ ተርፎም ለህልፈተ ህይወት ሊዳርግ እንደሚችል የህክምና ባለሙያዎች ማስጠንቀቂያ እየሰጡ ይገኛሉ። የአፍንጫ ጸጉርን መንቀል በአፍንጫ ውስጥ በሚገኙ ጥቃቅን የጸጉር ስሮች ላይ ቁስለት በመፍጠር ባክቴሪያዎች በቀላሉ ወደ ደም ስር እንዲገቡ መንገድ እንደሚከፍት ተነግሯል።
በህክምናው ዘርፍ "The Danger Triangle" ወይም "አደገኛው የፊት ሶስት ማዕዘን" ተብሎ በሚጠራው ቀጠና ውስጥ የሚገኘው የአፍንጫ ክፍል፣ የደም ስሮቹ በቀጥታ ከጭንቅላት (አንጎል) የደም ዝውውር ጋር የተያያዙ ናቸው። በዚህ ምክንያት በአፍንጫ ውስጥ የሚፈጠር ማንኛውም ኢንፌክሽን በቀጥታ ወደ ጭንቅላት በመሰራጨት "ካቨርነስ ሳይነስ ትሮምቦሲስ" (Cavernous Sinus Thrombosis) ለተባለ እጅግ አደገኛ የደም መርጋት ችግር ሊዳርግ ይችላል ነው የተባለው።
ምንም እንኳን ይህ አይነቱ አደጋ የመከሰት እድሉ ዝቅተኛ ቢሆንም፣ የሚከተላቸው የጤና እክሎች ግን እጅግ አስከፊ መሆናቸውን ዶክተሮች ያስረዳሉ። የአፍንጫ ጸጉር ተፈጥሯዊ ተግባሩ አቧራና ተህዋሲያን ወደ ሳንባ እንዳይገቡ መከላከል በመሆኑ፣ ጸጉሩን ነቅሎ ማስወገድ ይህንን የሰውነት የመከላከያ ስርአትም ጭምር እንደሚያዳክም ይነገራል።
ስለሆነም ባለሙያዎች የአፍንጫ ጸጉርን ከመንቀል ይልቅ በልዩ መቁረጫዎች (Trimmers) ወይም በንጹህ መቀስ ማሳጠር እጅግ አስተማማኝ መሆኑን ይመክራሉ። ይህ መረጃ በተለይ ለግል ንጽህናቸው ከፍተኛ ትኩረት ለሚሰጡ ወጣቶችና ጎልማሶች ትልቅ ጥንቃቄ የሚሻ ጉዳይ ሆኗል።
seledadotio

3 months ago