Logo
FIDEL POST NEWS
ኢትዮጵያ የተቀቀለ ስጋን ወደ ቻይና ለመላክ የሚያስችላትን ደረጃ ማዘጋጀቷ ተገለፀ

ኢትዮጵያ በአሁኑ ወቅት የስጋ ምርት ተቀባይ ሀገራትን ቁጥር ለመጨመር እና ከዘርፋ ያላትን ተጠቃሚነት ለማሳደግ አቅዳ እየሰራች ትገኛለች ሲል የግብርና ሚኒስቴር አስታውቋል። በሚኒስቴሩ የእንስሳት ምርት ሬጉላቶሪ መሪ ሥራ አስፈጻሚ ዶክተር አያሌው ሹመት ለብስራት ሬድዮ እንደገለፁት ኢትዮጵያ ካላት የእንስሳት ቁጥር አንፃር ምርትን ለውጪ ገበያ የመላክ  ፍላጎት አላት።

አሁን ላይ የሀገራትን  የምርት ጥራትና ደህንነት መስፈርትን በማሟላቷ የስጋ ምርቷን ኤክስፓርት ለማድረግ አቅዳ እየሰራች እንደምትገኝ ተናግረው ቻይና ከእነዚህ ሀገራት መካከል ተጠቃሽ ናት ብለዋል።በአብዛኛዉ የስጋ ምርቷን ጥቂተ በሆኑ የገልፍ ሀገራት ላይ ለሽያጭ የምታቀርበው ኢትዮጵያ የተቀቀለ የበግና የፍየል ስጋን ወደዚህች ለመላክ መዘጋጀቷ ተገልጿል።

ይህን እውን ለማድረግ ቻይና ስታነሳው ለነበረው የህግ ክፍተት ምላሽ መስጠት የሚያስችል ስራ መሰራቱ ተጠቅሷል።ኢትዮጵያ የቆየ ህግን ስትከተል በመቆየቷ የቻይናን የጥራትና ደህንነት መስፈርት በጠበቀ መልኩ ምርትን መላክ እንዲቻል ጥረት ሲደረግ መቆየቱን ያስረዱት ዶክተር አያሌው አሁን ላይ ለዚህ የሚረዳ ስታንዳርድ መዘጋጀቱን ተናግረዋል።

በአሁኑ ወቅት ኢትዮጵያ ይህን ምርት ወደ ቻይና ለመላክ ከምትችልበት የመጨረሻው ደረጃ ላይ መድረሷን ጠቁመው በዚህ አመት መጨረሻ ላይ የመግባቢያ ሰነድ ስምምነት እንደምትፈራረም ዶክተር አያሌው ጨምረው ለጣቢያችን ገልፀዋል።

በቅድስት ደጀኔ
#ዳጉ_ጆርናል
5 months ago

No replys yet!

Be the first to share what you think — your comment will appear here.