Logo
Getu Temesgen
በ5 ዓመቱ የውድድር መኪና መንጃ ፈቃድ በማግኘት ዓለምን ያስገረመው ቻይናዊ ታዳጊ
#ethiopia | አብዛኞቹ ሕፃናት ገና መራመድና መጫወት በሚለማመዱበት ዕድሜ፣ ይህ ታዳጊ ግን የፍጥነት ዓለምን ተቀላቅሏል። ቻይናዊው ሻኦ ዚያን ገና በ5 ዓመቱ የባለሙያ የውድድር መኪና አሽከርካሪነት ብቃት ማረጋገጫ ፈቃድ በማግኘት አዲስ የዓለም ታሪክ አስመዝግቧል።

የሻኦ ድንቅ ጉዞ የተጀመረው ገና በአንድ ዓመቱ የመኪና መንዳት ልምምድ መሣሪያዎችን (Simulators) በመጠቀም ሲሆን፣ ሦስት ዓመት ሳይሞላው ደግሞ የውድድር ካርቶችን (Go-karts) መንዳት ጀምሮ ነበር። ተሰጥኦው ከዕድሜው በላይ መሆኑን ያሳየው ታዳጊው፣ በ4 ዓመቱ በቻይና የራሊ ስፕሪንት ሻምፒዮና ላይ በመሳተፍ "የተስፋ ኮከብ" ሽልማትን ለመውሰድ በቅቷል።

ለዚህ ስኬት የአባቱ ድጋፍ ከፍተኛ ሲሆን፣ ለልጃቸው ብቃት ማሳደጊያ የሚሆኑ ዘመናዊ መለማመጃዎችንና የራሊ መኪናዎችን ለማቅረብ ከ116 ሺህ ዶላር በላይ ወጪ አድርገዋል። የሚገርመው ደግሞ አባትየው በውድድሮች ላይ የልጃቸው ረዳት አሽከርካሪ በመሆን አብረውት ይሳተፋሉ።

ሻኦ በ2023 ከቻይና አውቶሞቢልና ሞተር ሳይክል ፌዴሬሽን ይፋዊ የብቃት ማረጋገጫ ምስክር ወረቀት በመቀበል በሀገሪቱ ታሪክ ትንሹ ፈቃድ ያለው አሽከርካሪ ሆኗል።
ቴክኖሎጂውንም ጎን ለጎን በማስኬድ በዓለም አቀፍ የዲጂታል መኪና ውድድሮች ከምርጥ 30 አሽከርካሪዎች ተርታ መሰለፍ ችሏል።

ይህ ታዳጊ ከብዙ አዋቂዎች የተሻለ የመንዳት ብቃት ቢኖረውም፣ የሀገሪቱን የትራፊክ ሕግ ለማክበር ሲባል በመደበኛ የሕዝብ መንገዶች ላይ መንዳት አይፈቀድለትም። በዚህም ምክንያት የውድድር መኪኖቹ ወደ ሜዳ የሚወሰዱት በጭነት መኪና ተጭነው መሆኑን ኦዲቲ ሴንትራል ዘግቧል።

Getu Temesgen - (ጌጡ ተመስገን)
#getutemesgen #getu #ጌጡ #shaoxian #racingprodigy #china #youngestdriver #rally #automotivenews #talent #inspiration #futurestar

3 months ago

No replys yet!

Be the first to share what you think — your comment will appear here.