3 months ago
“ያለ አሜሪካም እርዳታ የዓለም መሪ መሆን ይቻላል!” ቢ.ዋይ.ዲ (BYD)
#ethiopia | የዓለማችን ግዙፉ የኤሌክትሪክ መኪና አምራች ቢ.ዋይ.ዲ (BYD)፤ የአሜሪካ ገበያ ባይኖርም በዓለም አቀፍ ደረጃ ስኬታማነቱን ለማስቀጠል እንደሚችል በልበ ሙሉነት አስታወቀ።
በቤጂንግ ዓለም አቀፍ የመኪና ኤግዚቢሽን ላይ ንግግር ያደረጉት የኩባንያው ስራ አስፈፃሚ ስቴላ ሊ፤ "በአሁኑ ወቅት የአሜሪካ ገበያ ለእኛ እንደ አማራጭ የታሰበ አይደለም" በማለት የኩባንያውን አቋም ግልጽ አድርገዋል።
እንደ ስራ አስፈፃሚዋ ገለጻ፣ ቢ.ዋይ.ዲ የአሜሪካ ገበያ ዝግ ቢሆንበትም በሌሎች የዓለም ክፍሎች ባለው ከፍተኛ ፍላጎት ውጤታማነቱን እያረጋገጠ ነው።
ኩባንያው ፊቱን ከአሜሪካ በማዞር በአሁኑ ወቅት በዋናነት ትኩረት ያደረገባቸው ቀጠናዎች፦
ብራዚል፦ በላቲን አሜሪካ ያለውን ከፍተኛ ፍላጎት ለመጠቀም።
ብሪታንያ እና አውሮፓ፦ ጥብቅ የአካባቢ ጥበቃ ህግ ባለባቸው በእነዚህ ቀጠናዎች የገበያ ድርሻውን ለማስፋት።
እስያ፦ በገዛ ቤቱና በአጎራባች አገራት ያለውን የበላይነት ለማጠናከር።
ቢ.ዋይ.ዲ በአሁኑ ወቅት በሽያጭ መጠኑ ቴስላን ጭምር በመብለጥ የዓለማችን ቀዳሚው የኤሌክትሪክ መኪና አምራች መሆኑ ይታወቃል። ይህ የኩባንያው በራስ መተማመን ደግሞ የዓለም አቀፉ የመኪና ኢንዱስትሪ መልክ እየተቀየረ መሆኑን ማሳያ ተደርጎ ተወስዷል።
Getu Temesgen - (ጌጡ ተመስገን) #getutemesgen #getu
#byd #electricvehicle #greenenergy #chinatech #automotivenews #globalmarket #sustainability

5 months ago
በ5 ዓመቱ የውድድር መኪና መንጃ ፈቃድ በማግኘት ዓለምን ያስገረመው ቻይናዊ ታዳጊ
#ethiopia | አብዛኞቹ ሕፃናት ገና መራመድና መጫወት በሚለማመዱበት ዕድሜ፣ ይህ ታዳጊ ግን የፍጥነት ዓለምን ተቀላቅሏል። ቻይናዊው ሻኦ ዚያን ገና በ5 ዓመቱ የባለሙያ የውድድር መኪና አሽከርካሪነት ብቃት ማረጋገጫ ፈቃድ በማግኘት አዲስ የዓለም ታሪክ አስመዝግቧል።
የሻኦ ድንቅ ጉዞ የተጀመረው ገና በአንድ ዓመቱ የመኪና መንዳት ልምምድ መሣሪያዎችን (Simulators) በመጠቀም ሲሆን፣ ሦስት ዓመት ሳይሞላው ደግሞ የውድድር ካርቶችን (Go-karts) መንዳት ጀምሮ ነበር። ተሰጥኦው ከዕድሜው በላይ መሆኑን ያሳየው ታዳጊው፣ በ4 ዓመቱ በቻይና የራሊ ስፕሪንት ሻምፒዮና ላይ በመሳተፍ "የተስፋ ኮከብ" ሽልማትን ለመውሰድ በቅቷል።
ለዚህ ስኬት የአባቱ ድጋፍ ከፍተኛ ሲሆን፣ ለልጃቸው ብቃት ማሳደጊያ የሚሆኑ ዘመናዊ መለማመጃዎችንና የራሊ መኪናዎችን ለማቅረብ ከ116 ሺህ ዶላር በላይ ወጪ አድርገዋል። የሚገርመው ደግሞ አባትየው በውድድሮች ላይ የልጃቸው ረዳት አሽከርካሪ በመሆን አብረውት ይሳተፋሉ።
ሻኦ በ2023 ከቻይና አውቶሞቢልና ሞተር ሳይክል ፌዴሬሽን ይፋዊ የብቃት ማረጋገጫ ምስክር ወረቀት በመቀበል በሀገሪቱ ታሪክ ትንሹ ፈቃድ ያለው አሽከርካሪ ሆኗል።
ቴክኖሎጂውንም ጎን ለጎን በማስኬድ በዓለም አቀፍ የዲጂታል መኪና ውድድሮች ከምርጥ 30 አሽከርካሪዎች ተርታ መሰለፍ ችሏል።
ይህ ታዳጊ ከብዙ አዋቂዎች የተሻለ የመንዳት ብቃት ቢኖረውም፣ የሀገሪቱን የትራፊክ ሕግ ለማክበር ሲባል በመደበኛ የሕዝብ መንገዶች ላይ መንዳት አይፈቀድለትም። በዚህም ምክንያት የውድድር መኪኖቹ ወደ ሜዳ የሚወሰዱት በጭነት መኪና ተጭነው መሆኑን ኦዲቲ ሴንትራል ዘግቧል።
Getu Temesgen - (ጌጡ ተመስገን)
#getutemesgen #getu #ጌጡ #shaoxian #racingprodigy #china #youngestdriver #rally #automotivenews #talent #inspiration #futurestar

Comments