Logo
Getu Temesgen
ላኪፔይ "ራስ" በተሰኘ ''AI'' የሚታገዝ መተግበሪያ በይፋ አስተዋወቀ
#ethiopia | የኢትዮጵያን የዲጂታል ፋይናንስ ዘርፍ በአዲስ መልክ ይቀይረዋል የተባለለት ላኪፔይ ፋይናንሺያል ቴክኖሎጂስ፣ በሰው ሰራሽ አስተውሎት የተደገፈ እና በድምፅ ትዕዛዝ የሚሰራ የክፍያ መተግበሪያውን መጋቢት 4 ቀን 2018 ዓ.ም በሳይንስ ሙዚየም አስመርቋል። ከፍተኛ የመንግስት የስራ ሃላፊዎች በታደሙበት በዚህ ደማቅ የምረቃ ስነ-ሥርዓት ላይ፣ የዕለቱ ዋነኛ ትኩረት የነበረው "ራስ" የተሰኘው አዲሱ የAI ረዳት ቴክኖሎጂ ነው።

ይህ መተግበሪያ ለተጠቃሚዎች የሚሰጣቸው አገልግሎቶች የሚከተሉት ናቸው፦

ደንበኞች በአማርኛ፣ በኦሮምኛ እና በትግርኛ ቋንቋዎች በድምፃቸው ብቻ በማዘዝ የባንክ እና የተለያዩ የክፍያ አገልግሎቶችን ማግኘት ይችላሉ። ይህ አሰራር ዘመናዊ ስልኮችን ለመጠቀም ለሚቸገሩ እንዲሁም ማንበብና መጻፍ ለማይችሉ የህብረተሰብ ክፍሎች የፋይናንስ አገልግሎትን በቀላሉ ተደራሽ ያደርጋል።

መተግበሪያውን ውጤታማ ለማድረግ ላኪፔይ ከኦሮሚያ ባንክ ጋር በዋና ስትራቴጂካዊ አጋርነት እየሰራ ይገኛል። በተጨማሪም "ላንዲ ግሎባል" ከተባለ ዓለም አቀፍ የቴክኖሎጂ ኩባንያ ጋር ባደረገው ስምምነት፣ ተጠቃሚዎች በማስተርካርድ አማካኝነት ዓለም አቀፍ ክፍያዎችን በቀላሉ መፈጸም ያስችላቸዋል ተብሏል።

መተግበሪያው ከገንዘብ ዝውውር በተጨማሪ የህንጻ አስተዳደርን እና የአከራይ-ተከራይ መረጃን የሚያቀናጅ ማህደር አካቷል።

እንዲሁም ነጋዴዎች ከደንበኞቻቸው ጋር በቀጥታ በቪዲዮ በመገናኘት ገበያቸውን የሚያሰፉበት ነጻ የቪዲዮ ግንኙነት አገልግሎትንም ይዟል።

እ.ኤ.አ. በየካቲት 2025 ከኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ የክፍያ ሥርዓት አከናዋኝነት ፈቃድ ማግኘቱ የሚታወሰው ላኪፔይ፣ አሁን ይዞት ብቅ ያለው ዘመናዊ የAI ቴክኖሎጂ በሀገሪቱ እያደገ ለመጣው የዲጂታል ኢኮኖሚ ትልቅ ሚና እንደሚኖረው ይጠበቃል።

Getu Temesgen - (ጌጡ ተመስገን)
#getutemesgen #getu #ጌጡ #lakipay #ላኪፔይ #artificialintelligence #ai #digitalfinance #ethiopia #rasai #digitalethiopia #techinethiopia #fintech

7 months ago

No replys yet!

Be the first to share what you think — your comment will appear here.