Logo
YenetaTube
አዶናይ ለታላቅ ሰብዓዊ ተግባር ወደአሜሪካ ተጓዘ

የኸርት ቱ ኸርት ቺልድረንስ ኤይድ ፋውንዴሽን
(Heart to Heart Children's Aid)
የበጎ ፈቃድ አምባሳደር ወጣት አዶናይ ብርሃነ ለልብ ሕሙማን ሕፃናት ድጋፍ ለማሰባሰብ ተልእኮ ወደዩናይትድ ስቴት አሜሪካ አቀና።

ወጣት አዶናይ፤ በኸርት ቱ ኸርት ቺልድረንስ ኤይድ ፋውንዴሽን አስተባባሪነት ከነገ ቅዳሜ ማርች 14 (መጋቢት 5/2018) ከ 2:00 Pm ጀምሮ ለኢትዮጵያውያን የልብ ሕሙማን ሕጻናት መርጃ የሚውል ገቢ የማሰባሰብ ቻሌንጅ የሚጀመር ሲሆን ማርች 21 (መጋቢት 12/2018) በዋሽንግተን ዲሲ ማርዮት ሆቴል በሚከናወን የማጠቃለያ ኘሮግራም እንደሚጠናቀቅ አቶ ብርሃን ተድላ የፋውንዴሽኑ መሥራችና የኢትዮ ኢስታንቡል ሆስፒታል ዋና ሥራ አስፈጻሚ አስታውቀዋል።

በገቢ ማሰባሰቢያ መርሐግብሩ ላይ በአሜሪካን ሀገር የሚኖሩ ኢትዮጵያውያን እና የኢትዮጵያ ወዳጆች የበኩላቸውን አስተዋጵኦ በማድረግ የልብ ሕሙማን ሕጻናት ተገቢውን የሕክምና ድጋፍ እንዲያገኙ ያግዙ ዘንድ አቶ ብርሃን ጥሪ አቅርበዋል።

የኢትዮ ኢስታንቡል አጠቃላይ ሆስፒታል እስካሁን ለ113 ሕፃናት ከ120 ሚሊዮን ብር በላይ በሆነ ወጪ የነፃ የልብ ቀዶ ጥገና ማድረጉን ያስታወሱት አቶ ብርሃን ይኸ ታላቅ ስራ በአንድ ተቋም ብቻ የሚከናወን ባለመሆኑ በኸርት ቱ ኸርት ቺልድረንስ ኤይድ ፋውንዴሽን በኩል ተጨማሪ የወገን ድጋፍ ለማግኘት ይኸ ፕሮግራም መዘጋጀቱን ጠቁመዋል።

በአሁኑ ወቅት በኢትዮጵያ ከ25 ሺ በላይ የልብ ሕሙማን ሕጻናት ሕክምና ለማግኘት እየተጠባበቁ እንደሚገኙ መረጃዎች ያሳያሉ።

7 months ago

No replys yet!

Be the first to share what you think — your comment will appear here.