Logo
YenetaTube
የሐዘን መግለጫ - #ከኢዜማ

በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ጋሞ ዞን ደጋማ ቀበሌያት በደረሰ መሬት መደርመስና ጎርፍ እስካሁን የ 64 ዜጎች ሕይወት ማለፉ የዜና አውታሮች ገልፀዋል።

ኢዜማ በዚህ አደጋ ሕይወታቸውን ባጡ ዜጎች የተሠማውን ጥልቅ ሐዘን እየገለፀ ለቤተሰብ እና ወዳጆቻቸው መፅናናትን ይመኛል።

ቀደም ብሎ ይህ ዓይነት የተፈጥሮ አደጋ በቀድሞ አወቃቀር ደቡብ ክልል ውስጥ ይገኙ የነበሩ ቦታዎች በተለያየ ጊዜ ተመሳሳይ የመሬት ናዳና ጎርፍ የሚያሰተናግዱ ሲሆን አደጋዎቹ ከፍተኛ ጉዳትን ሲያደርሱ በተደጋጋሚ ተመልክተናል።

መንግሥት እንዲህ ዓይነት አደጋዎችን ለመከላከል የሚያስችሉ ቅድመ አደጋ መለያ ቴክኖሎጂዎችን መጠቀምና፣ መሠል ተፈጥሯዊ አደጋዎች እንዳይፈጠሩ የሚያደርጉ የአካባቢ ጥበቃ ሥራዎችን ማለትም ሕብረተሰቡን ያሳተፈ የችግኝ ተከላ፤ ናዳውን የሚከላከሉ የግንባታ ሥራዎች (retention walls) ተግባራዊ ማድረግ እንዲሁም ዜጎችን ተደጋጋሚ አደጋ ከሚደርስባቸው አከባቢዎች በማንሳት በተሻሉ ቦታዎች እንዲኖሩ ማድረግ እና መሠል ተግባራትን መፈፀም ላይ ዕየታየ ያለውን ድክመት በማረም፤ በየዓመቱ መሰል አሳዛኝ ክስተቶችን መከላከል የሚያስችል እርምጃ በመውሰድ የዜጎችን ሕይወት ከአደጋ መከላከል ይጠበቅበታል፤ በተጨማሪም አደጋዎቹ ከተከሰቱ በኋላ ጉዳቱን መቀነስ የሚያስችሉ ተግባራትን በማከናወን የዜጎችን ደኽንነት እንዲጠብቅ እንጠይቃለን።

ዜጎችና ተቋማት ለተጎጂዎችና ቤተስቦቻቸው ሰብዓዊ ድጋፍ እንዲያድርጉ ጥሪ እያቀረብን የሚፈፀሙ ማንኛውም ሰብዓዊ ተግባራት ሕግን ባከበረ፣ ለተጎጂዎች መድረሱን በሚያረጋግጥ እና ግልፅነት በተሞላበት መልኩ መሆን እንዳለበት ለመግለጽ እንወዳለን።

በድጋሚ የተሠማንን ጥልቅ ሐዘን እየገለጽን ለሟች ቤተሰብ እና ወዳጆቻቸው ቶሎ መጽናናትን እንመኛለን።
#ኢዜማ

5 months ago

No replys yet!

Be the first to share what you think — your comment will appear here.