Logo
Getu Temesgen
የአባታቸውን መንበር ለመረከብ የተቃረቡት ቀጣዩ የኢራን መሪ ማን ናቸው?
#ethiopia | የኢራን መንፈሳዊ ጠቅላይ መሪ አሊ ኻሜኒን ለመተካት በሚደረገው የሥልጣን ሽግግር ሂደት ውስጥ የልጃቸው የሞጅታባ ኻሜኒ ስም በጉልህ እየተነሳ ይገኛል።

በሀገሪቱ ፖለቲካዊ እና ሃይማኖታዊ መዋቅር ውስጥ ከፍተኛ ተጽዕኖ እንዳላቸው የሚነገርላቸው ሞጅታባ፣ በተለይም አባታቸውን ለመተካት ዋነኛው ዕጩ እንደሆኑ የብዙዎች ግምት ነው።

እንደ አውሮፓውያን አቆጣጠር በሴፕቴምበር 1969 በሰሜናዊ ምስራቅ ማሽሃድ ከተማ የተወለዱት ሞጅታባ፣ ከአሊ ኻሜኒ ስድስት ልጆች መካከል ሁለተኛው ናቸው።

የመጀመሪያ እና ሁለተኛ ደረጃ ትምህርታቸውን በቴህራን በሚገኘው ታዋቂው 'አላቪ' ሃይማኖታዊ ትምህርት ቤት የተከታተሉ ሲሆን፣ ገና በ17 ዓመታቸው በኢራን-ኢራቅ ጦርነት ወቅት በውትድርና ውስጥ ለአጭር ጊዜያት ማገልገላቸው ይነገራል።

ይህ የጦርነት ተሳትፎ ለኢራን አገዛዝ መጠናከርና ለምዕራባውያን ያላቸውን ጠንካራ አቋም ለመቅረጽ ትልቅ ሚና እንደነበረው ይታመናል።

ከጦርነቱ በኋላ በ1999 የሃይማኖት ትምህርታቸውን ለመቀጠል ወደ ሺዓ ሥነ-መለኮት ማዕከል 'ቁም' ያቀኑት ሞጅታባ፣ ምንም እንኳን እስካሁን የሃይማኖት መሪዎች የሚለብሱትን የክብር ልብስ (Turban) ባይለብሱም፣ ከበስተጀርባ በኢራን የደህንነትና የፖለቲካ መዋቅር ውስጥ ትልቅ ስልጣን እንዳላቸው ይነገራል። አሁን ላይ የኢራን ቀጣይ መሪ ማን ይሆናል? ለሚለው ጥያቄ የብዙዎች አይን በሞጅታባ ላይ አርፏል።

Getu Temesgen - (ጌጡ ተመስገን)
#getutemesgen #getu #ጌጡ #bisratfm #ኢራን #ሞጅታባ_ኻሜኒ #አሊ_ኻሜኒ #የፖለቲካ_ዜና #መካከለኛው_ምስራቅ #iran #mojtabakhamenei #news

3 months ago

No replys yet!

Be the first to share what you think — your comment will appear here.