ትራምፕ የኢራንን ቀጣይ መሪ በመምረጥ ሂደት ላይ መሳተፍ አለብኝ ሲሉ ተናገሩ
የዩናይትድ ስቴትስ ፕሬዚዳንት ዶናልድ ትራምፕ የሀገሪቱን ከፍተኛ መሪ ህልፈት ተከትሎ የኢራንን ቀጣይ መሪ በመምረጥ ረገድ በግላቸው መሳተፍ እንዳለባቸው እንደሚያምኑ ተናግረዋል። ትራምፕ ከአክሲዮስ ጋር ባደረጉት ቃለ ምልልስ ኢራን ያለ አሜሪካ ተሳትፎ ተተኪ ለመሾም ብትሞክር "ጊዜዋን ታባክናለች" ብለዋል።
የተገደለው የጠቅላይ መሪ አሊ ካሜኔይ ልጅ ሞጅታባ ካሜኒ በብዙዎች ዘንድ ዋንኛ ተተኪ ተደርጎ ይታያል፣ነገር ግን ትራምፕ ውጤቱን እንደማይቀበሉት ተናግረዋል። "የካሜኔይ ልጅ ቀላል ክብደህ ነው" ያሉት ትራምፕ ፤ "በሹመት ሂደት ውስጥ መሳተፍ አለብኝ" ብለዋል።
ትራምፕ የቀድሞውን አመራር ፖሊሲዎች የሚያስቀጥሉ ማንኛውንም አዲስ የኢራን መሪ እንደማይቀበሉ በመግለጽ ይህንን ማድረጉ ከአሜሪካ ጋር “በአምስት ዓመታት ውስጥ” እንደገና ግጭት እንደሚያመጣ አስጠንቅቀዋል። "የካሜኔይ ልጅ በእኔ ዘንድ ተቀባይነት የለውም፤ ለኢራን ስምምነት እና ሰላም የሚያመጣ ሰው እንፈልጋለን" ብለዋል።
በስምኦን ደረጄ
#ዳጉ_ጆርናል

5 months ago