Logo
YenetaTube
የሰሜን ኮሪያው መሪ ኪም ጆንግ ኡን ቀጭን ማስጠንቀቂያ ሰጡ

የሰሜን ኮሪያው መሪ ኪም ጆንግ ኡን በአሁኑ ወቅት በኢራን ውስጥ በሚገኙ ዜጎቻቸው ላይ ማንኛውም አይነት ጉዳት ቢደርስ ሀገራቸው በቀጥታ ወደ ጦርነቱ እንደምትገባ ለአለም አቀፉ ጥምረት ጠንከር ያለ ማስጠንቀቂያ አስተላልፈዋል። መሪው የዜጎቻቸው በሰላም መመለስ "ለድርድር የማይቀርብ" ጉዳይ መሆኑን ገልጸውንይህም ቀጣናዊ ግጭቱን ወደ ኑክሌር ኃያላን ፍጥጫ ሊቀይረው የሚችል አደገኛ ሁኔታ መፍጠሩ ተነግሯል።

ይህ ማስጠንቀቂያ የተሰማው የእስራኤሉ ጠቅላይ ሚኒስትር ቤንያሚን ኔታንያሁ "ኢራን ማለት 50 ሰሜን ኮሪያ ማለት ናት" በማለት የቀጣናውን ስጋት ከገለጹ በኋላ ነው ይህ አባባል በተፋላሚ ወገኖች መካከል ያለውን ጥልቅ የርዕዮተ-ዓለም ልዩነት በግልጽ ያሳየ ሆኗል።

ኢኮኖሚያዊ እና ወታደራዊ ቀውሶች
የዓለም ጦርነት ስጋት እያየለ በመጣበት በዚህ ወቅት
* ኳታር፦ በሀገሪቱ የድንገተኛ ጊዜ አዋጅ የታወጀ ሲሆን የጋዝ ምርት ሙሉ በሙሉ ተቋርጧል።

* ስፔን፦ ከአሜሪካ ጋር ለትብብር የተስማማችው በንግድ ታሪፍ (tariffs) ከፍተኛ ጫና ከደረሰባት በኋላ እንደሆነ ተገልጿል።

* ወታደራዊ ኪሳራ፦ በኢራን የባህር ኃይል ላይ እየደረሰ ያለው ጥቃት ቀጥሏል። በተለይም የኢራን የጦር መርከብ እና IRIS Fateh የተሰኘችው ሰርጓጅ መርከብ መጥለቃቸው ወታደራዊ ውጥረቱን ጣሪያ አስነክቶታል።

*ምንም እንኳን የአሜሪካ ኮንግረስ ተጨማሪ ጥቃቶችን ለማገድ ድምጽ ቢሰጥም ፔንታጎን ለደረሰበት የ2 ቢሊዮን ዶላር የመሳሪያ ኪሳራ ማካካሻ 50 ቢሊዮን ዶላር ተጨማሪ በጀት እየጠየቀ ይገኛል።

የሩሲያ እና የናቶ (NATO) እንቅስቃሴ
ሩሲያ ከቴህራን መሪዎች ጋር ያላት ግንኙነት በመቋረጡ የኢራንን የኑክሌር ጣቢያዎች ለመቆጣጠር ዝግጅት እያደረገች መሆኑ ተሰምቷል። በሌላ በኩል በቱርክ የሚገኘው የናቶ የአየር መከላከያ ሥርዓት የባሊስቲክ ሚሳኤል ካከሸፈ በኋላ ከፍተኛ ጥንቃቄ ላይ ይገኛል።

በአሁኑ ወቅት "ኦፕሬሽን ኤፒክ ፉሪ" ከቀጣናዊ ጣልቃ ገብነት ወደ ዓለም አቀፋዊ ግጭት የመሸጋገር አዝማሚያ እያሳየ ነው። በኢራን የሚገኙ የሰሜን ኮሪያ ዜጎች ጉዳይ ለዚህ ግዙፍ ጦርነት መቀስቀሻ ሊሆን እንደሚችል ተሰግቷል።

5 months ago

No replys yet!

Be the first to share what you think — your comment will appear here.