ከእስራኤል ጋር የተደረገው ስምምነት እና ክልላዊ አለመረጋጋት በሶማሊላንድ የበርበራ ወደብ ላይ አሉታዊ ተጽዕኖ ሊያሳድር ይችላል ተባለ
ሶማሊላንድ በእስራኤል እውቅና ማግኘቷ ለበርበራ ወደቧ ትልቅ ጥቅም እንደሚኖረው ትናገራለች።
ነገር ግን በክልሉ ሚሳዔሎች እየተተኮሱ ባለበት በአሁኑ ወቅት ወደቡ የጥቃት ኢላማ ሊሆን ይችላል የሚል ስጋት አለ።
በኤደን ባሕረ ሰላጤ ላይ የሚገኘው የበርበራ ወደብ፤ ባለፉት አስርት ዓመታት ውስጥ በተባበሩት አረብ ኤምሬትስ ኩባንያ (DP World) አማካኝነት በዓለም ላይ ካሉ ሥራ የሚበዛባቸው የንግድ መስመሮች አንዱ ሆኖ ቆይቷል፡፡
በርበራ አሁንም ከአጎራባች ጅቡቲ ወይም ሞምባሳ ያነሰ የኮንቴነር አገልግሎት የሚሰጥ ቢሆንም፤ የወደብ ትራፊክ መጠኑ ከ2023 እስከ 2025 በ30 በመቶ አድጓል፤ የቅርብ ጊዜ የዲፕሎማሲ እንቅስቃሴዎችም ይህንን ይበልጥ ሊያሳድጉት ይችላሉ ተብሏል፡፡
ከ130 ሚሊየን በላይ ህዝብ ካላትና የባህር በር ከሌላት ጎረቤት ኢትዮጵያ ጋር ድርድር ላይ ያለው የስምምነት ሂደት የወደብ ትራፊክን በሌላ 80 በመቶ ሊያሳድግ እንደሚችል የወደብ ባለስልጣን ዳይሬክተር አሊ ዲሪዬ አህመድ ተናግረዋል።
ሶማሊላንድ በ1991 ራሷን ነጻ አገር ብላ ካወጀች በኋላ እውቅና የሰጠች የመጀመሪያዋ ሀገር የሆነችው የእስራኤል ውሳኔ "ከፍተኛ ጭማሪ" እንደሚያመጣ ዳይሬክተሩ ገልጸው፤አሁኑኑ የወደብ ማስፋፊያ እቅድ በማውጣት ላይ መሆናቸዉን አንስተዋል፡፡
በአሜሪካ እና በእስራኤል በኢራን ላይ የተፈጸመው ጥቃት የክልላዊ ጦርነት ስጋትን በጨመረበት በዚህ ወቅት ከእስራኤል ጋር ያለው ጥምረት አደጋዎችንም ያስከትላል ተብሏል፡፡
በየመን የሚገኘው እና በኢራን የሚደገፈው የሁቲ አማፂ ቡድን መሪ አብደል ማሌክ አል-ሁቲ፤ በሶማሊላንድ ውስጥ ማንኛውም ከእስራኤል ጋር የተገናኘ ጉዳይ እንደ "ወታደራዊ ኢላማ" እንደሚቆጠር ቀደም ሲል አስጠንቅቀዋል።
በዚህ ሳምንት መጨረሻ በኢራን ሚሳዔሎች ኢላማ የተደረገችው የተባበሩት አረብ ኤምሬትስ፤ የበርበራ ወደብን ከማስተዳደሯም በላይ በቅርቡ ያስፋፋችው ወታደራዊ ካምፕ በአቅራቢያው ይገኛል።
ባለሙያዎች እንደሚናገሩት፤የተባበሩት አረብ ኤምሬትስ ሶማሊላንድ በእስራኤል እውቅና እንድታገኝ ቁልፍ ሚና የተጫወተች ሲሆን፤የእስራኤል ኃይሎች በበርበራ ወታደራዊ ካምፕ ውስጥ አስቀድመው ሊገኙ እንደሚችሉ ይገመታል።
አንድ ምዕራባዊ ዲፕሎማት ለኤኤፍፒ የዜና ወኪል በሰጡት ቃል፤‹‹በሀገሪቱ ውስጥ የእስራኤል ወታደራዊ ቡድን ወይም የደህንነት አካል እንደሚገኝ ሰፊ ግምት አለ››ብለዋል፤ ሆኖም ማንኛውም ወታደራዊ ትብብር በሚስጥር እንደሚቆይ ይጠበቃል።
በኤምሬትስ ካምፕ ውስጥ የእስራኤል ወታደራዊ ቡድን ወይም ደህንነት መኖሩ ከተረጋገጠ ወደቡ ለሁቲ ወይም ለኢራን ሚሳዔሎች ተጋላጭ ሊሆን ይችላል።
በተጨማሪም የአልቃይዳ ተባባሪ የሆነው የሶማሊያው አል-ሸባብ፤ እስራኤል ሶማሊላንድን ለመጠቀም የምታደርገውን ማንኛውንም ጥረት እንደሚቃወም በመግለጽ በአካባቢዉ ስጋት ፈጥሯል።
የፖለቲካ ተንታኞች እና ምሁራን የሶማሊላንድ ባለስልጣናት ‹‹ስለ ወደፊቱ ጊዜ ሳያስቡ እውቅናውን ብቻ ነው ያዩት›› ሲሉ ስጋታቸውን ገልጸዋል።
እስከዳር ግርማ

3 months ago