Logo
FIDEL POST NEWS
የኤፕስታይን አስከፊ ሚስጥር፦ ገዳይም ነበር? የልጃገረዶች አስከሬን ፍለጋ ተጀመረ

​የቢሊየነሩ ጄፍሪ ኤፕስታይን የክፋት ታሪክ አሁንም አላበቃም። አዳዲስ መረጃዎች እንደሚያመለክቱት፣ ኤፕስታይን ከህፃናት ዝውውር ባለፈ ነፍሰ ገዳይም ሳይሆን አይቀርም የሚል ስጋት ነግሷል።

በኒው ሜክሲኮ የሚገኘው የፍትህ ሚኒስቴር፣ በኤፕስታይን ግዙፍ እርሻ ውስጥ የልጃገረዶች አስከሬን ተቀብሯል በሚል ምርመራውን በድጋሚ ከፍቷል።

​ይህ እርምጃ የተወሰደው ከሦስት ሚሊዮን በላይ የሚሆኑ የኤፍ.ቢ.አይ ሚስጥራዊ ሰነዶች ይፋ መደረጋቸውን ተከትሎ ነው።

በአንድ ሰነድ ላይ የቀድሞ የኤፕስታይን ሰራተኛ እንደገለጸው፣ ሁለት የውጭ ሀገር ዜግነት ያላቸው ልጃገረዶች በኤፕስታይን እና በባልደረባው ጊሌን ማክስዌል ትዕዛዝ ተገድለው በእርሻው ግቢ ውስጥ ተቀብረዋል።

ልጃገረዶቹ የተገደሉት "በጭካኔ በተሞላ የፆታ ጥቃት" ወቅት በገመድ ታንቀው እንደሆነም ምስክሩ ገልጿል።

​የኒው ሜክሲኮ ባለስልጣናት እነዚህን ዘግናኝ ወንጀሎች የሚያረጋግጡ የቪዲዮ ማስረጃዎችን እና ያልተበረዙ ሰነዶችን ለመሰብሰብ እየሰሩ ይገኛሉ።

በአንድ ወቅት እንደ አስፈሪ ፊልም ይታዩ የነበሩት "ሰይጣናዊ ድርጊቶች" አሁን ወደ እውነትነት እየተቀየሩ መምጣታቸው አለምን እያነጋገረ ይገኛል።

ምርመራው በሂደት ላይ ሲሆን፣ ተጨማሪ አስከሬኖች ሊገኙ እንደሚችሉ ይጠበቃል።
3 months ago

No replys yet!

Be the first to share what you think — your comment will appear here.