ከኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ቋሚ ሲኖዶስ የተሰጠ የኃዘን መግለጫ
‹‹እለ ሐሙ በእንተ ስሙ፤ ምድር ሠናይት ርስቶሙ
ስለስሙ መከራን የተቀበሉት፤ መንግሥተ ሰማያት የእነርሱ ናት››
(ማቴ 5÷51 ፤ ቅዱስ ያሬድ)
ከዚህ በፊት በአርሲ ሀገረ ስብከት በተለያዩ ወረዳዎች የበርካታ ኦርቶዶክሳውያን ወገኖቻችን ሕይወት በመጥፋቱና ከሞት የተረፉትም ከቤት ንብረታቸው ተፈናቅለው ወደ አጎራባች ከተሞች ተሰደው ለረሀብና ለእርዛት ተጋልጠው እየኖሩ መሆኑ ይታወቃል፡፡
ቀደም ሲል በተለያዩ ጊዜያት፣ በደረሰው ሞትና ስደት ምእመናን እያዘነ ባሉበት፣ እኛም ከኃዘናችን ባልተጽናናንበት ሁኔታ ጥቃቱ በአዲስ መልኩ ቀጥሎ የ21 ንጹሐን ወገኖቻችን ሕይወት በግፍ ማለፉን፣ በሕይወት የተረፉትም በታጣቂዎቹ መታገታቸውንና የደረሱበት አለመታወቁን፣ h10 የሚበልጡ አባውራዎች ቤትና ንብረት እንደተቃጠለ በመግለጽ ከሀገረ ስብከቱ የቀረበውን ሪፖርት የተመለከትነው ጥልቅ በሆነ ኃዘን ነው፡፡
አገር ሰላም ብለው በሚኖሩት ከምንም ጉዳይ ጋር ንክኪ በሌላቸው ኦርቶዶክሳውያን ልጆቻችን ላይ ይህን አስነዋሪ ድርጊት የፈጸሙት አካላትም ግድያውን በሃይማኖት ስም ይፈጽሙት እንጂ የሃይማኖት ስዎች ግን አይደሉም፡፡ ዓላማቸውም በሀገራችን ለረዥም ዘመናት ተከባብረው አብረው በኖሩት የሃይማኖት ተቋማት መካከል ግጭትን መፍጠር ነውና የእስልምና ሃይማኖት ተከታዮችና ሕዝበ ክርስቲያኑ በጋራ ልናወግዛቸው ይገባል፡፡
በመሆኑም በወገኖቻችን ላይ የተፈጸመው አሰቃቂ ግድያ በሕዝበ ክርስቲያኑ ዕለታዊ ኑሮ አሉታዊ ተጽዕኖ የሚፈጥር፣ በቅዱሳት መጻሕፍትም ሆነ በሰው ልጅ ሰብአዊ አኗኗር ፈጽሞ ተቀባይነት የሌለው አጸያፊ ድርጊት በመሆኑ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን ቋሚ ሲኖዶስ በጽኑ አውግዞታል፡፡
በምሥራቅ አርሲ ሀገረ ስብከት በተደጋጋሚ እየተፈጸመ ያለው ሞትና መፈናቀልም ኦርቶዶክሳውያን ልጆቻችን በየትኛውም የሀገራችን ክፍል በነጻነት ሠርተው የመኖርና ሥርዓተ አምልኮ የመፈጸም ሕገ መንግሥታዊ መብታቸውን የሚጋፋ በመሆኑ የክልሉና የፌዴራል መንግሥት ጉዳዩን በልዩ ሁኔታ ተከታትለው አፋጣኝ መፍትሔ እንዲሰጡበት ቋሚ ሲኖዶስ በጥብቅ ያሳስባል፣
ፍርድን በመሻት የሚጮኸው ስለስሙ መከራን የተቀበሉት የንጹሐን ደም ተገቢውን ፍትሕ ይፈልጋልና ይህን አስነዋሪ ድርጊት የፈጸሙት አካላት በሕግ እንዲጠየቁ፣ ወደፊትም ክቡር የሆነው የሰው ልጅ ሕይወት እንዳይጠፋ፣ የዜጐች ሀብትና ንብረት እንዳይወድም መንግሥት የዜጎችን ደኅንነት የማስጠበቅ ተግባሩን እንዲያከናውን ቋሚ ሲኖዶስ ጥሪውን በአጽንኦት ያስተላልፋል፤
በደረሰው አደጋ ዙሪያ ተነጋግሮ ተገቢውን ውሳኔ ለማስተላለፍ የተሰበሰበው ቋሚ ሲኖዶስም የአካባቢው ችግር አስተማማኝ በሆነ መንገድ ተፈትቶ ዘላቂ ስላም እስኪገኝ ድረስ በቅዱስ ሲኖዶስ ምልዐተ ጉባኤ የተሰየመው የሀገር ሰላምና የቤተ ክርስቲያን አንድነት ዐቢይ ኮሚቴ ከፌደራልና ከክልሉ መንግሥት ጋር በመነጋገር ሥራውን አጠናክሮ እንዲቀጥልና የሚመለከታቸውም አካላት በየድርሻቸው አስፈላጊውን ትብብር እንዲያደርጉ ቋሚ ሲኖዶስ በክብር ያሳስባል፡፡
የክልሉ መንግሥትና የአካባቢው መስተዳድርም ችግሩን ለመፍታት እያደረገ ያለው ጥረት አጠናክሮ እንዲቀጥልና ወደፊትም ችግሩ እንዳይደገም ከመሠረቱ መፍታት የሚያስችል እርምጃ እንዲወስድ ቅድስት ቤተ ክርስቲያናችን ትጠይቃለች፡፡
በመጨረሻም ስለስሙ በሥጋቸው መከራን በመቀበል ሕይወታቸውን በአጡት ኦርቶዶክሳውያን ልጆቻችን የተሰማንን መሪር ኃዘን እየገለጽን ልዑል እግዚአብሔር ዕረፍተ ነፍስን እንዲሰጥልን፣ ቤተሰቦቻቸውንም እንዲያጽናናልን እንጸልያለን፡፡
የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ቋሚ ሲኖዶስ
የካቲት 2018 ዓ/ም አዲስ አበባ ኢትዮጵያ

4 months ago