ዓለም አይታው የማታውቀውን መሣሪያ አሜሪካ ላይ አዘንባለው - ኢራን
በመካከለኛው ምስራቅ እየተካሄደ ባለው መጠነ ሰፊ ጦርነት፣ የኢራን አብዮታዊ ዘበኛ (IRGC) ከፍተኛ አዛዥ ጄኔራል ኢብራሂም ጃባሪ አሜሪካንና እስራኤልን የሚያስደነግጥ አዲስ መግለጫ ሰጥተዋል።
ጄኔራሉ ኢራን እስካሁን የተጠቀመችው አሮጌ የሚሳይል ክምችቷን ብቻ መሆኑን በመጥቀስ፣ በቀጣይ ግን ዓለም አይታው የማታውቀውን “ሚስጥራዊና ዘመናዊ መሣሪያ” እንደምትጠቀም ዝተዋል።
"እስካሁን የተኮስነው የቆሻሻ ብረት ነው" ብለዋል።
ጄኔራል ጃባሪ ለሀገር ውስጥ መገናኛ ብዙኃን በሰጡት መግለጫ፣ አሜሪካ በኢራን ከፍተኛ አመራሮች ላይ የሰነዘረችውን "ኦፕሬሽን ኤፒክ ፉሪ" (Operation Epic Fury) አጣጥለውታል።
"ጠላቶቻችን በፈጸሙት ጥቃት ተደስተው ይሆናል፤ ነገር ግን እኛ እስካሁን ለአፀፋ የተጠቀምነው በእኛ እይታ እንደ 'ቆሻሻ ብረት' (Scrap Metal) የምንቆጥራቸውንና ጊዜ ያለፈባቸውን አሮጌ ሚሳይሎች ነው" ብለዋል።
ኢራን ወደፊት ስለምትጠቀመው መሣሪያ ዝርዝር መረጃ ባይሰጡም፣ ጄኔራሉ የሚከተለውን አስደንጋጭ ማስጠንቀቂያ አስተላልፈዋል፦
“እውነተኛው ጦርነት ገና አልጀመረም፤ ኢራን ለዓመታት በሚስጥር ያዘጋጀቻቸው፣ በራዳር የማይታዩና በየትኛውም የዓለም ክፍል ያለን ኢላማ የመምታት አቅም ያላቸው እጅግ ዘመናዊ የቴክኖሎጂ ውጤቶች ዝግጁ ናቸው። አሜሪካና እስራኤል ሊገምቱት የማይችሉት ጥፋት ይጠብቃቸዋል” ብለዋል።
seledadotio

3 months ago