Logo
Getu Temesgen
''በቀጠናችን ላሉ ሀገራት አለኝታ፣ መከታ፣ ጋሻ ለመሆን ነው''

📌የኢፌዴሪ ጦር ኃይሎች ጠቅላይ አዛዥ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ካስተላለፉት መልዕክት የተወሰደ
#ethiopia | ✅ ታሪክ ከማይዘነጋው የመለዮ ለባሽ የአዲስ ምሩቃን፣ በተለይም በርከት ያሉ ሴት አየር ወለዶች የተመረቁበትን በዓል በጋራ በሀዋሳ ከተማ ለማክበር በመገናኘታችን የተሰማኝን ታላቅ ደስታ ልገልጽላችሁ እወዳለሁ።

✅ “የእኛ ተልዕኮ ራዕይ ያለው ለትውልድ የሚሻገር ሁነኛ ተቋም መፍጠር ነው። የእኛ ተልዕኮ ውጊያ የሚያስቀር፣ ውጊያ የሚጨርስ Elite Force መገንባት ነው።

✅ የእናንተ ተልዕኮ ኢትዮጵያን መገንባት፣ ኢትዮጵያን መጠበቅ፣ ኢትዮጵያን ማጽናት እና ኢትዮጵያን ማሸጋገር ነው።”

✅ ኢትዮጵያ በልጆቿ ላብ ትሰራለች፣ ኢትዮጵያ በልጆቿ አጥንት እና ደም ትጸናለች፤ ኢትዮጵያ አልተደፈረችም አትደፈርም፤ በክብር እና በነጻነት ለልጆቻችን የምናሸጋግራት ብቸኛዋ የአፍሪካ ፈርጥ ሆና ትቀጥላለች።

✅ የእኛ ዝግጅት በድፍን አፍሪካ ሰላም ለማረጋገጥ፣ በድፍን አፍሪካ ብልጽግናን ለማረጋገጥ፣ በቀጠናችን ላሉ ሀገራት አለኝታ፣ መከታ፣ ጋሻ ለመሆን ነው።

Getu Temesgen - (ጌጡ ተመስገን)
#getutemesgen #getu #ጌጡ #ebc

8 months ago

No replys yet!

Be the first to share what you think — your comment will appear here.