Logo
Getu Temesgen
እንኳን ደስ አላችሁ ~ እንኳን ደስ አለን !
#ethiopia | “የኮምትኬስ ካርኩ ( ሚዛን- አማን ) ዓለም አቀፍ አውሮፕላን ተብሎ እንዲሰየም በሙሉ ድምፅ በምክር ቤት ፀደቀ ፦

የሚዛን -አማን ከተማ አሥተዳደር ምክር ቤት የሚዛን አማን ከተማ ዓለም- አማቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ በቀኝ አዝማች ኮምትኬስ ካርኩ ሥም እንዲሠየም አፀደቀ።

የሚዛን- አማን አስተዳደር ምክር ቤት 4ኛ ዙር 18ኛ ዓመት የሥራ ዘመን 34ኛ መደበኛ ጉባኤ በተለያዩ አጀንዳዎች ሲመክር ቆይቷል።

ጉባኤው የቀኛዝማች ከምትኬስ ጋርኩ እና የልጃቸው ግራዝማች ጃዊ ኮምትኬስ የሠሯቸው የልማት ስራዎች ከተማዋ ዛሬ ላይ ለመድረስ መሠረት የጣሉ መሆናቸው ተገልጿል።

ለሕዝብ ሥለ አበረከቷቸው የአርበኝነት እና የልማት ሥራ በሚዛን- ቴፒ ዩንቨርስቲ ተቋም ጥናትና ምርምር ተደርጎ በሚለከታቸው አካላት እየተተቸ መሆኑ ተጠቁሟል።

በተለይ የቤንች ምድር በትራንስፓርት ያለመኖር ከማዕከላዊ መንግስት የራቁ መሆናቸው መነሻ በማድረግ ቦታቸውን በመፍቀድ የአውሮፕላን ማረፊያ እንዲሠሩ ያደረጉ ናቸው።

አዲስ እየተገነባ በመጠናቀቅ ላይ የሚገኘው የሚዛን አማን ዓለም አቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ በሥማቸው እንዲሠየም ቀርቦ ምክር ቤቱ መክሮበታል።

በዚህ መሠረት አዲሱ ዓለም አቀፍ የአውሮፕላን ማረፊያው “የሚዛን- አማን ኮምትኬስ ካርኩ ዓለም አቀፍ የአውሮፕላን ማረፊያ” ተብሎ እንጢጠራና እንዲሠየም በሚዛን- አማን ከተማ ምክር ቤቱ አባላት በሙሉ ድምፅ ፀድቋል።

ጌታመሳይ ሙሉጌታ ~ (Getamesay Mulugeta)

3 months ago

No replys yet!

Be the first to share what you think — your comment will appear here.