በጋምቤላ ክልል የእስረኞች የምግብ አቅርቦት በቀን 75 ብር እንዲከፈል ተደረገ
በጋምቤላ ክልል የእስረኞች የመሰረታዊ ፍላጎቶች አቅርቦትና አገልግሎት አሰጣጥን ለማሳደግ ጥረት መደረጉን የክልሉ ፍትህ ቢሮ አስታውቋል።የክልሉ አቃቢ ህግ አቶ ተመስጌን ካሳ ለብስራት ሬድዮ እንደተናገሩት ባለፋት ስድስት ወራት በክልሉ የእስረኞች የምግብ አቅርቦት 41ነጥብ 79 ብር የነበረውን ወደ 85 ብር ለማድረስ ታቅዶ ነበር።
በዚህም የእስረኞች የምግብ አቅርቦት በቀን 75 ብር እንዲከፈል ተደርጓል በማለት ተናግረዋል።እንደዚሁም በአራቱም ማረሚያ ቤቶች በተለያዩ የመንግስት መስሪያ ቤቶች እና ለጋሽ ድርጅቶች ለእስረኞች የቁሳቁሶች ድጋፍ ለማድረግ ታቅዶ እንደነበር አቃቤ ህጉ ገልፀው ይህም በዕቅዱ መሰረት መከናወኑን አብራርተዋል።
የህግ ታራሚ ደህንነትና ሰብአዊ መብቶች አያያዝን ለማጠናከር እና 85 በመቶ ለማድረስ ታቅዶ 75 በመቶ ማድረስ ተችሏል።በሌላ በኩል በአራቱም ማረሚያ ቤቶች የእስረኞች አያያዝን አስመልክቶ በሚመለከታቸው አካላት ለ120 እስረኞች ጉብኝት ለማድረግ ታቅዶ ለ85 ታራሚዎች ጉብኝት ተደርጓላቸዋል ሲል ቢሮው ጨምሮ ገልጿል።
ቅድስት ደጀኔ
#ዳጉ_ጆርናል

6 months ago