Logo
SeledaPost
በሻሸመኔ የቀድሞ ፍቅረኛዬን አገባክ በሚል ቅናት ተነሳስቶ የገዛ ጓደኛውን የገደለው ወጣት በ22 ዓመት እስራት ተቀጣ

👉የሟች እሬሳ በአውሬ ተበልቶ ነበር

​በአሩፋ ክፍለ ከተማ "ቻይና ካፕ" ተብሎ በሚጠራው አካባቢ ለዓመታት ጓደኛሞች የነበሩት  እና  ዳፋ መካከል የተፈጠረ ቅናት ለሞት አድርሷል።

ተከሳሽ የ25 ዓመቱ ሀብታሙ የቀድሞ ፍቅረኛ የነበረችው ልጅ  የ27 ዓመቱ ኮርሜ ገልገሉ ህጋዊ ባለቤት መሆኗ ቅናት አሳድሮበት ​ኮርሜ ገልገሉ ገሎ በድንገት ከአካባቢው ተሰወረ።

የሟች ቤተሰቦቹ ለፖሊስ ልጃቸው መጥፋቱን ለፖሊስ አሳውቀው ፖሊስ ፍለጋ ላይ እያለ በአካባቢው ጫካ ውስጥ በአውሬ የተበላ የሰው ቅሪተ አካል ይገኛል።

​ፖሊስ የቀረውን ጥቂት ቅሪተ አካል በማንሳትና ከቤተሰብ ደም በመውሰድ ባደረገው የDNA ምርመራ፣ ቅሪተ አካሉ የጠፋው የኮርሜ ገልገሉ መሆኑን አረጋግጧል።

​የሻሸመኔ ከተማ አስተዳደር ከፍተኛ ፍርድ ቤት የካቲት 26 ቀን 2018 ዓ.ም በዋለው ችሎት ​ተከሳሽ ሀብታሙ ዳፋ በፈፀመው ከባድ የሰው መግደል ወንጀል ጥፋተኛ ሆኖ በመገኘቱ በ22 ዓመት ፅኑ እስራት እንዲቀጣ ወስኖበታል።

seledadotio.
seledadotio
8 months ago

No replys yet!

Be the first to share what you think — your comment will appear here.